መስቀል እና የጉራጌ ህዝብ

መስቀል በአል በኢትዮጲያ ከሚከበሩ ታላላቅ ሃይማኖታዊ በአሎች መሃል አንዱ ነው። ከአዲስ አመት ጋር ተያይዘው የሚመጡ የትምህርት እና የመሳሰሉ ወጪዎች እና ከአዲስ አመት ክብረ በአል ሁለት ሳምንት በኋላ መምጣቱ በሚያሳድረው የኢኮኖሚ ጫና ምክንያት የቤቱ አከባበር ቀዝቀዝ የሚል ቢሆንም ፤ በዋዜማው ያለው ልዩ የዳመራ ስርዓት በአሉን የደመቀ እና የተለየ ያደርገዋል። በጧፍ እና በሻማ የሚታገዘው ይህ የዳመራ አከባበር ስርዓቱን የሚያደምቀው ሲሆን ዳመራው ወዴት እንደወደቀ በማየት የመጪውን አመት ሁኔታ መተንበይ ሌላው ገጽታው ነው።

የመስቀል በአል ሲነሳ በብዛት አብሮ የሚነሳው ነገር ቢኖር አዲስ አበባን እና ሌሎች ከተሞችን ጥሎ ወደ ትውልድ አገሩ በመጓዝ ቤተሰቡ ጋር በአሉን የሚያሳልፈው የጉራጌ ህዝብ ነው። ይህ ከታወቀው የንግድ ችሎታቸው ቀጥሎ የጉራጌ ህዝቦችን የሚለያቸው ስርዓት ነው። የመስቀል በአል በጉራጌ ህዝብ ከስምንት ቀናት እስከ አንድ ወር የሚያክል ገዜ የሚከበር በአል ነው። እያንዳንዱ ቀን የተለያየ ስም ያለው ሲሆን በየቀኑ የተለያዩ አይነት ምግቦችን በመብላት እና ከቤተሰብ ጋር ጥሩ ግዜ በማሳለፍ ያልፋል። በመጀመሪያዎቹ ቀናት ይህ ስርዓት የሴቶችን እና የተክሎችን ህይወት ፈጣሪነት የሚያስታውስ ሲሆን በበአሉ ዝግጅት የቤቱ እማወራ የሚኖርባትን ጫና በመረዳት በመጀመሪያ ለሷ ተበሎ በተዘጋጀ ፕሮግራም ቤተሰቦቿ ሲንከባከቧት እና ምግብ ሲያዘጋጁላት ይቆያሉ። በሚቀጥለው ቀን እናቶች የሚያስፈልገውን በመገዛዛት የተለመደውን የጎመን እና አይብ ክትፎ ያዘጋጃሉ። የወንዶች ቀን ቀጣይ የሚመጣ ሲሆን በጸሎት የሚጀምር የበሬ እርድ ይደረግና ያ እጅ የሚያስቆረጥመው ክትፎ ይዘጋጃል። በስተመጨረሻ በአዛውንት ምረቃት እና በቀጣዩ አመት ለመገናኘት በመመኘት በአሉ ይጠናቀቃል።

መልካም የመስቀል በአል ለክርስትና እምነት ተከታዮች

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s