ተራራ እንስራ

ሆላንዶች አንድ አባባል አላቸው ፤ “እግዚአብሄር ምድርን ሰራ እኛ ደግሞ ሆላንድን ሰራናት” ። ይህን የሚሉት ካለምክንያት አይደለም። አብዛኛው የሃገሪቱ ክፍል ጠፍጣፋ እና ከባህር ጠለል በታች ሆኖ አገሪቷ ከባህር አጠገብ ብትሆንም ፤ የሆላንድ መሃንዲሶች አገሪቷን ከማንኛውም የውሃ መጥለቅለቅ የሚከላከል ግድብ ሰርተዋል። በተጨማሪም በጣም ትንሽ ቦታ ላይ ብዙ ህዝብ ሰላላቸው ውቅያኖስ እና ባህር አሸሽተው እና መሬት በማድረግ ለመኖሪያነት በመጠቀማቸው ነው። ልክ በዱባይ እንዳሚሰሩት ዘንባባ ቅርጽ ደሴቶች ማለት ነው።

ይህ ሰው ሰራሽ አገር ውስጥ ከጥቂት ሳምንታት በፊት አንድ ጋዜጠኛ በዓምዱ ላይ አንድ ሃሳብ ይሰነዝራል ፤ ይኅውም ከልጅነቱ ጅምሮ በሆላንድ ተራራ እንደሚኖር ያስብ እንደነበር እና በአገሪቱ ተራራ ሰለሌለ ተራራ ለመውጣት እና በረዶ ላይ ለመንሸራተት ሌላ አገር በመሄድ ሆላንዶች ብዙ ወጪ ሰለሚያወጡ ፤ ተራራ መስራት ቢቻል ጥሩ እንደሚሆን ነበር። ብዙዎች ሃሳቡን ቅዥት ነው ብለው ቢተዉትም ፤ ጥቂቶች መስራት እንደሚቻል አምነው ከጸሃፊው ጋር ሃሳቡን ማዳበር ጀመረዋል። በአስገራሚ ሁኔታ ቻይናና ህንድን ጨምሮ በተለያዩ አገሮች የሚኖሩ ባለሃብት ፕሮጀችቱን ለመደገፍ ፍላጎታቸውን ያሳዩ ሲሆን ተራራውን ለመስራት ክ 72 እስከ 432 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ሊጠይቅ እንደሚችል ተገምቷል።

እኛም ሃሳብ አለን ፤ ኢትዮጲያ ተራራ ኤክስፖርት ማድረግ ብትችል ጥሩ የገቢ ምንጭ ይሆናል።

[ABC News]

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s