የሳምንቱ ቪዲዮዎች

ከተወሰነ መጥፋት በኋላ ለናንተ የተመረጡ የሳምንቱ ቪዲዮዎች ጀባ ብለናል።

ሞተር ሳይክልን በመቶዎች ሜትር የሚቆጠር ከፍታ ያለው ተራራ ጫፍ ላይ መንዳት እጅግ አስፈሪ ሲሆን በበረዶ የተሸፈነ ተራራ ሲሆን ደግሞ ሞትን በቅርብ እርቀት ከቻልከኝ ያዘኝ እንደማለት ነው።

በእንሰሳ ማቆያ ያለ ግዙፍ አንበሳ ሊበላት ሲሞክር የማይደነግጥ ልጅ ማየት ይፈለጋሉ? እንዴታ አሉ አይደል መቼም።

ከአሁን በኋላ ለዘመናዊ ኮንስትራክሽን ወደ ምዕራቡ አለም ማየት ሊያቆም እንደሆነ ማስረጃ የሚሆን ቪዲዮ ነው ቀጣዩ። ቻይኖች 30 ህንጻ ፎቅ ከመሰረት እስከ መጨረሻ ሰራዎች በ15 ቀናት ብቻ አጠናቀው አለምን ጉድ አሰኝተዋል።

ቡድኑን ለማበረታት የተሰየመ አሻንጉሊት ለባሽ በሚያሳየው ትርኢት የትምህርት ቤቱን ንብረት አውድሞ ፕሮግራሙ ለመቋረጥ ተገዷል። ተመልካቹ ከትርኢቱ ይበልጥ መሰበሩ ያስደሰተው ይመስላል።

እንደ እግር ኳስ ከተመልካች ጀርባ ሳይሆን ሜዳ አጠገብ የሚቀመጡ የቅርጫት ኳስ ጨዋታ ዘጋቢዎች ከሚያጋጥማቸው ችግሮች አንዱ በሴቶች ዳንስ ሃሳባቸው ተሰርቆ መንተባተባቸው ነው። እርግጠኛ ነኝ ቪዲዮውን ሲያዩ እርሶም ሃሳቦ ተሰርቆ እሱ የሚለውን እንደማይሰሙት።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s