ዓለም በ2100

የባቡር የ100 አመት ለውጥ

የባቡር የ100 አመት ለውጥ

በሲቲ ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ኒው ዮርክ የምናባዊ ፊዚክስ ፕሮፌሰር የሆኑት ሚቺዮ ካኩ በየካቲት 2012 ገበያ ላይ በሚውል Physics of the Future: How Science Will Shape Human Destiny and Our Daily Lives by the Year 2100 በሚሰኝ መጽሃፋቸው ላይ ከ300 በላይ ታዋቂ ሳይንቲስቶችን ካነጋገሩ በኋላ በ2100 ዓ.ም በዓለም ላይ ሊኖሩ የሚችሉ ግኝቶችን ተንብየዋል። ከትንበያዎቹ መካከል የተወሰኑት እነዚህ ናቸው።

1. የሃይድሮጅን ሀይል
በአሁኑ ግዜ በሰፊው የምንጠቀማቸው አላቂ የሆኑትም ሆነ አረንጓዴ ቴክኖሎጂ የሚባሉት የሃይል ምንጮች በቅርብ ግዜ ከኑክሌር በተሻሉ ከሃይድሮጅን ቲክኖሎጂ ይተካሉ። በ2019 ፈረንሳይ ውስጥ የሚመረቅ የምርምር ጣቢያ ዘርፉን የበለጠ ያጠናክረዋል ተብሎ ይጠበቃል።

የሃይድሮጅን

ሃይድሮጅን

2. የህዋ አሳንስር
በ1900 ዓ.ም የሰው ልጅ ከ100 አመት በኋላ ገንዘብ እየከፈለ ወደ ህዋ ሽርሽር መውሰድ ይችላል ቢባሉ እንደሚሳለቁበት ግልጽ ነው። እና ይሄንንም ትንበያ ላይ መሳቅ ይቻላል። በጠንካራ ቁሳቁስ በሚሰራ አሳንስር የህዋ ሽርሽር እውን እንደሚሆን ይታመናል።

3. እርጅናን ማስቆም
የዲኤንኤ(DNA) ቴክኖሎጂ ብዙዎች እንደሚያስቡት የቅርብ ግዜ ቴክኖሎጂ ሳይሆን በ19ኛው ክፍለ ዘመን የተጀመረ ነው። በብዙ ለውጦች ውስጥ ያለፈው ይህ ቴክኖሎጂ በአሁኑ ግዜ በህክምና፣ በመድሃኒት ስራ፣ በወንጀል ምርመራ ውስጥ ትልቅ ድርሻ ይዟል። ከእርጅና ጋር በተያያዘ በዲኤንኤ ላይ የሚደረጉ ምርምሮች እንጅና የሚያመጣውን ጂን በመለየት እና ስራውን በማስቆም የሰው ልጅ እንዳያረጅ ያግዛል ተብሎ ይጠበቃል።

[cnn]

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s