ፍቅር በአማርኛ

ባሳለፍነው ሳምንት ማክሰኞ የዋለው የቫለንታይን ቀን በፍቅረኛሞች ተከብሮ ፤የፍቅር ጓደኛ በሌላቸው ደግሞ ለመረሳት ተሞክሮ አልፎአል። ቀኑን ምክንያት በማድረግ ኢትዮጲያውያን ፍቅራቸውን በደብዳቤ እንዴት እንደሚገልጹት ለማሳየት የተወሰኑ የፍቅር ደብዳቤዎችን ይዘናል።

———————————————————————————————————————————

መቼም ገና ብዕሬን ከወረቀት ጋር ሳገናኝ እኔ የተሰማኝን በግልጽ እና ጉልህ ቃል ስገልጽልሽ በጭንቀት ሲሆን አንቺ ደሞ ይህ ወረቀት አጭር እና ግልጽ መልክት አዘል የምን የማን እና ከማን እንደመጣ ተረድተሽ ከአንቺ አንደበት የሚወጣውን መልስ በቃልም ሆነ በወረቀት እስክሰማው ድረስ ጭንቀቴ ይህ ነው አልልሸም።

ይኅው ያንቺን አይኖች ከተመለከትኩበት ቀን ጀምሮ ንጹህና አፍቃሪ ልቤ ውስጥ ገብተሽ እስካሁኗ ሰአት ድረስ መኖር ብቻ ሳይሆን አለመኖርም ልጀምር ዳር ዳር እያለኝ ነው። በዚች ምድር ላይ ገና አለም ሲፈጠር አዳምን ለሄዋን እንዳዘዘ ሁሉ እኔም ላንቺ ሳልሆን የቀረሁ አይመስለኝም። ግን እኮ ፍቅሬ ምን አለ በዚች አለም ሲኖር በልቶ ጠጥቶ ተደስቶ ሲኖር ሞት የሚባል ቀጣፊ ተዘጋጅቷል። ፍቅር ብሎ እውነተኛ ፍቅርን በልባችን ለዘላለም ተክሎ አፍቃሪ ብለን የምንመኘው (የምንይዘው) በዚግዜያዊ ጥቅም ተታሎ ቃሉን አጥፎ ሲጓዝ ለአፍቃሪው የምንግዜም የህሊና ቁስል ሆኖ ይቆይበታል። ታዲያ ፍቅሬ በዚህ ምድር በህይወት ስቆይ ፍቅርን ላፍቃሪዎች ትቼ በብቸኝነት ለመኖር እራሴን አዘጋጅቼ ነበር። መቼም ሰው ነኝና ተሸነፍኩ ባንቺ እምቡጥ ፍቅር ለዘላለም አምቄ እኖራለሁ ያልኩትን የልጅነት ፍቅሬን ባንድ ቀን እይታ ባንድ ቀን የልቤን ውስጥ ቁልፍ ስፍራ ተረከብሽው።

ይህን ሁሉ ስገልጽልሽ ላንቺ ምን እንደሚሰማሽ አላቅም። ፍቅሬ እወድ… አልጨርስም ። “ለምን” ትይኝ ይሆናል ። ሰው ነኝና ከመጠን ያለፈ ደስታን እሻለሁ ካንቺ ጋር። ግን መልስሽ ለኔ ምን እንደሆነ አሁንም ሰላልገባኝ ነው።

ብቻ ብዙ ሃተታ አላበዛም ባጭሩ ፍቅር ፣ እውነተኛ ፍቅር ፍቅር ፍቅር … እስከ አለም ፍጻሜ ድረስ በብቸኛው ልቤ አፈቀርኩሽ …

I love you. I will love you.

የአንቺን መልስ ማክሰኞ በማንኛውም ሰአት እጠብቃለሁ።

———————————————————————————————————————————

በጣም ለምወድሽ እና ለማፈቅርሽ xxxxዬ

እንደማር የምትወደጂ እንደ ሎሚ የምትመጠጪ ውድ እህቴ እንደምን አለሽልኝ? በመጀመሪያ የከበረ ሰላምታዬን እያቀረብኩ በምድር ላይ ያለ ነገር ሁሉ ጥሩ ጥሩ ላንቺ እየተመኘሁ ያንቺው አፍቃሪ xxxx። xxxxዬ እንዴት እንደምወድሽ ለመግለጽ ቃላት ያጥሩኛል። የወደድኩሽን ምክንያት እኔ እስካሁን የፈለግኩትን ጨዋ አስተዋይ (አሳቢ) ስለነበረ አንቺን በሁሉም ነገር ስላየሁሽ ነው። በአሁኑ ግዜ አይተህ አስተውለህ ካልፈቀርክ ዘላቂው ኪሳራ ብቻ ነው።

xxxxዬ እና አስቢበት እና መልስ በትንሽ ወረቀት በአጭር ግዜ እፈልጋለሁ እሺ። አደራ እሺ በይኝ ብቻ ከዛ በኋላ ብዙ ሰለፍቅራችን የማናግርሽ እና የማጫውትሽ ብዙ ቁምነገሮች አሉ።

አንድ ነገር ላስጠነቅቅሽ የምፈልገው ድብዳቤውን ማንም ሰው እንዲያየ አልፈልግም ምክንያቱም ብዙ ሴት ልጆች ሲለምኑኝ እኔ ትምህርቴን ካልጨረስኩ ሴት ጓደኛ የሚባል አልፈልግም ስላልኩኝ ታዲያ ልምን አሁን ድብዳቤ ጻፈ እንዳይሉኝ ነው። በተረፈ መልስ ብቅርብ ግዜ መልካም መልስ ያድርገው አሜን።

———————————————————————————————————————————–

ጃንሆይ በአንድ ወቅት “ሴት ልጅን ብትቀርባት ጥርሷ ቢስቅ አንሶላም ብትጋፈፋት ጡትዋን እንጂ ልቧን አታገኘውም” አሉ ይባላል። እውነት ጃንሆይ ይበሉት አይበሉት አላውቅም ግን ይህን አባባል እኔ አልተቀበልኩትም ምክንያቱም እንኳን ልቤን ኩላሊቴን እና ጉበቴን ሳትወስደው እንደማይቀር እጠራጠራለሁ።

xxxxዬ በእውነት አንተን መውደዴን ወደድኩት። ለነገሩ እግዚአብሄር ይወደኛል፤ ስለሚወደኝ የሚወድ ልብ ሰጠኝ። እነዛ ውል ውል የሚሉት አይኖችህ በሃሳቤ እየታዩኝ እንዴት እንደሚያረገኝ ብታውቅ ደስ ይለኝ ነበር። …….

ተጻፈ በxxxx

Advertisements

28 Comments

  1. ፍቅረኛዬ ጋር ተጣልተናል! ይቅርታ እንድታደርግልኝ ያሰብኩት ነገር የባሰ ለያየን:: ምን ላድርግ? እኔ አሁንም እወዳታለሁ:: እሳም እንደማትጠላኝ እርግጠኛ ነኝ:: በምን ልቅረባት?

  2. በጣም አሪፍ ነው::ያፈቀርካትን ሴት እንዴት ማሳመን እንዳለብህ ይረዳሃል “ደብዳቤ ፅፈህ መላኩ ይቅርና” ከዚ ደብዳቤ ቃላቶችን ተውሰህ ማሳመን ትችላለህ::

  3. ደብዳቤ በኛ ግዜ ቀረ። አስታወሳለሁ 9ኛ ክፍል ደብተሬ ውስጥ ያገኘሁት ደብዳቤ። ፍርሃት ሴትነት ደስታ ምን እንደተሰማኝ አላቅም ግን እሺ አልኩት ጓደኛሞች ሆነን ሃይስኩልን አሳለፍን ነው ሚባለው።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s