አንጋፋው ደራሲና ጋዜጠኛ ማሞ ውድነህ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

ይህ ሳምንት በኢትዮጲያ የስነጽሁፍ ታሪክ ውስጥ የጨለማ ሳምንት ሊባል የሚችል ነው። አንጋፋውን ስብሃት ገ/እግዚአብሄርን ባጣን በጥቂት ቀናት ውስጥ ሌላው ታላቅ ደራሲ ማሞ ውድነህ ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል። በጠና መታመማቸው በተለይ በሪፖርተር በሰፊው ሲዘገብ የነበረው ጋሽ ማሞ ባደረባቸው ሀመም ህክምናቸውን ሲከታተሉ ቆይተው አርብ የካቲት 23 2004 ዓ.ም በተወለዱ በ79 አመታቸው አርፈዋል።


የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበርን ለ12 ዓመት በፕሬዝዳንትነት የመሩት አቶ ማሞ የተተረጎሙ እና የራሳቸው ፈጠራ የሆኑ 53 መጽሃፎችን እና 8 ድራማዎችን ያዘጋጁ ሲሆን በተለይ የኛ ሰው በደማስቆ፣ የበረሃው ተኩላ እና የካይሮው ጆሮ ጠቢ የመሳሰሉ ሰለላ ላይ ያውጠነጠኑ መጽሃፎችን ለአንባቢዎች አድርሰዋል። አራዳኦንላይን ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን ይመኛል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s