ሃይሌ ገ/ስላሴ እንግሊዛዊቷ ፓውላ ራድክሊፍን በግማሽ ማራቶን አሸነፈ

በኦስትሪያ ዋና ከተማ ቪየና በተካሄድው ውድድር ላይ የተሳተፉት ሃይሌ ገ/ስላሴ እና የሴቶች ማራቶን ሪኮርድ ባለቤት ፓውላ ራድክሊፍ ብቻ ሲሆኑ ውድድሩ ሲጀመር ፓውላ የ 7ደቂቃ ከ 52 ሰከንድ ቅድሚያ ተሰጥቷት ነበር። ይህ ሰዓት በአትሌቶቹ በርቀቱ ያስመዘገቡት ምርጥ ግዜ መካከል ያለ ልዩነት በመሆኑ ውድድሩን እኩል ቢጀምሩ ሃይሌ ያለውን የበላይነት ያካካሰ ነበር።

ውድድር ተጀምሮ ሩብ ያህል ርቀት ሲቀራቸው ከኋላ የደረሰባት ሃይሌ ውድድሩን 60 ደቂቃ ከ 52 ሰኮንድ ሲያጠናቅቅ ሰሞኑን ብሮካይትስ ሲያማት የነበረችው ፓውላ በ 72 ደቂቃ 03 ሰኮንድ አጠናቃለች። ለለንዶኑ አሊምፒክስ ይውምታደርገው ዝግጅት አካል እንደሆኑ የተናገረችው ፓውላ ከ 70 ደቂቃ በፊት ለመግባት አስባ እንደነበር ግልጻለች።

“በጣም የሚያሰጋኝ ነገር ሰውነቴን ጥሩ ስሜት እየተሰማኝ አለመሮጤ ነው” ያለችው ራድክሊፍ መንፈሳዊ ጥንካሬዋን ሊጎዳት እንደሚችል ገልጻለች።

ይህ የተለየ ውድድር የተካሄደው ከአመታዊው የቪየና ማራቶን ጋር ሲሆን በማራቶኑ ውድድር በወድንዶቹ ሄንሪ ሱጉት ከኬንያ እና በሴቶቹ ፋጤ ቶላ ከኢትዮጲያ ማሸነፋቸው ታውቋል። [Reuters, Image via Telegraph]

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s