የትዳር ቀለበታቸውን እየደበቁ የሚወሰልቱ ሰዎችን የሚያጋልጥ ቀለበት ተሰራ

አንዳንዶች የትዳር አጋር ወይም እጮኛ ቢኖራቸውም ቀለበታቸውን እያወለቁ ብቸኛ በመምሰል በድብቅ ሌላ ሰው ማሳሳቅ ከዛም አልፎ መወስለት ይጀምራሉ። እነዚህ ሰዎች የተለየ የሚያረጋቸው የሚያታልሉት ባለቀለበት አጋራቸውንም አብረው የሚወሰልቱትን ሰውም መሆኑ ነው።

እና ከሰሞኑ አንድ ድርጅት ይህንን ለመከላከል ይረዳል ያለውን ጸረ-ውስለታ ቀለበት ለገበያ አቅርቧል። ከላይ ፎቶ ላይ እንደሚታየው ቀለበቱ በውስጥ በኩል አግብቻለሁ “I’m married” የሚል ጽሁፍ ያለበት ሲሆን በሚደረግ ግዜ ጣት ላይ በቀላሉ የማይጠፋ ምልክት ስለሚተው አውልቆ ሚስት/ባል የለኝም ማለት አዳጋች ያደርገዋል።

ይህን ቀለበት ማን ገዝቶ ለትዳር ጓደኛ እንደሚሰጥ ግራ ይገባል ምክንያቱም ቀለበቱ ከመታለል የሚያድነው አብሮ ለመወስለት የታሰበውን ሰው መሆኑ ነው። ብቻ ቀለበት እያረጉ እራሱ የሚያጭበረብሩ በበዙበት አለም ይሄንን ቀለበት ለመስጠት ከሚያሳስብ አጋር ይጠብቀን ነው። [Gawker]

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s