የአፍዝ አደንግዝ ሚስጥር

እድሜአቸው ጠና ያሉ አመቤት በዕለተ ሰንበት ወደተጠሩበት ድግስ እንደአቅማቸው ሽክ ብለው እየሄዱ ነው። የአንገት እና የጆሮ ወርቃቸው ፈካ ብሎ ሙሉ ሀበሻ ቀሚስ፣ ትከሻቸው ላይ ጣል የተደረገ ነጠላ እና ጸጉራቸውን የሚያምር ሹሩባ ተሰርተዋል። ሰው በዝቶ በሚቻኮልበት ጎዳና ቀስ ብለው የሚያዘግሙት እናት በስተ ግራ ትከሻቸውን ነካ የሚያረጋቸው ሰው ተሰምቷቸው ዞር ሲሉ አንድ ወጣት “እናቴ ስኳር የሚሸጥበትን ቦታ ያቁታል?” ብሎ ይጠይቃቸዋል። እንደማያውቁ ሊነግሩት አፋቸውን ሲከፍቱ ከፊትለፊት በስተቀኝ በኩል ትከሻቸውን ሌላ ሰው ይነካቸው እና ወደፊት በኩል ዞር ይላሉ። እናም ሌላ ወጣት “ማዘር የቀበሌ ሱቅ የት ጋር ነው?” ይላቸዋል። ከዛች ደቂቃ በኋላ ምን እንደተፈጠረ አያስታወሱም ብቻ ወርቆቻቸውን እያወለቁ ለወጣቶቹ ሲሰጡ ትዝ ይላቸዋል።

ከቦርሳቸው ሁላ ያላቸውን ገንዘብ አራግፈው ሰጥተው ልጆቹን ከሸኙ በኋላ ኪሳቸው ውስጥ የቀረች አንድ ብር እንዳላቸው ያስታወሱና የሚሄዱትን ልጆች ጠርተው ለትራንስፖርት እንኳን የምትሆናቸውን ገንዘብ ለወጣቶቹ ያስረክባሉ። እናም ከትወሰነ ግዜ በኋላ ከእንቅልፋቸው እንደ መባነን ይሉና በደንብ ማንነታቸውን ሲያስታውሱ አንድ አደባባይ አቅራቢያ ግድግዳ ተደግፈው ወርቃቸው ገንዘባቸው ተሰርቀው እንደሆነ ይረዱና ጩህታቸውን ያቀልጡታል። እና ሰዉ እንደምንም ተባብሮ ፖሊስም ደርሶ ነገሩን አረጋግቶ እናትየው ከቤተሰቦቻቸው ይገናኛሉ። እናም እንዴት እንደሆነ በማያቁት ሁኔታ ፈዘው ደንዝዘው ሌባዎቹ የሚሏቸውን ታዘው እንደተዘረፉ ተናገሩ።

እንደዚህ እና መሰል ሰዎችን በማፍዘዝ የሚሰሩ ወንጀሎች በአዲስ አበባ እና በተለያየ የሃገሪቱ ክፍሎች መስማት የተለመደ ነው። አፍዝ አደንግዝ ተበሎ የሚታወቀው ይህ ድርጊት በብዛት ከሃይማኖት እና ከጥንቆላ ነክ ነገሮች ጋር ይያያዛል። እኔም እስከ ቅርብ ግዜ ድረስ ነገሩን ከዛ ጋር በማያይዝ ሊተነተን የማችል ነገር ይመስለኝ ነበር። ነገር ግን ሰሞኑን እንዳረጋገጥኩት ይህ ሙሉ በሙሉ አደንዛዥ እጽዋትን እና ኬሚካሎችን በመቀላለቅ የሚደረግ ሳይንስ ነክ ነገር መሆኑን ነው።

ቫይስ የተባለ ድርጅት ሰሞኑን በአንድ ዱኩመንታሪ እንዳረጋገጠው ማፍዘዝን ሰው ላይ የሚያመጣው “ስኮፖላሚን” የተባለ አደገኛ አደንዛዥ ዕጽ ነው። በቅጽል ሰሙ “የሰይጣን ትንፋሽ” ተበሎ የሚታወቀው ዕጽ ቦጎታ ኮሎምብያ ውስጥ የሚታወቅ ሲሆን “ብሩዳንጋ” ከተባለ አትክልት አበባ እና ግንድ የሚዝጋጅ ነው። ከመጠጥ እና ከሌላ ነገሮች ጋር ጥሩ ስሜት አላቸው እንደሚባሉት ኮኬን እና ሄሮይን መደብ የማይመደበው ይህ ዕጽ ሙሉ በሙሉ ሰው የሚያዞትን ነገር እንዲፈጽሙ የሚያደርግ ነው። በብዛት ከተወሰደ እስከ ሞት ሊያደርስ የሚችለው ይህ እጽ ለማንበብ የተያዘ ወረቀት ላይ ከተገኘ እንኳን እንደሚያፈዝ ተደርሶበታል። እናም ኢትዮጲያ ውስጥም የተወሰኑ ሰዎች ተመሳሳይ ዕጽ የሚሰራበትን መንገድ ደርሰውበት እየተጠቀሙበት ነው ማለት ነው።

ተጨማሪ

– በኢትዮጲያ ውስጥ የሚገኘው እና አጠፋሪስ በመባል የሚታወቀው ተክል ብሩጋንዳ ከተባለው ከኮሎምቢያ ተክል ጋር በጣም የሚቀራረብ እና በአብዛኛው የአዲስ አበባ መንገዶች ላይ ጨምሮ የሚታይ ተክል ነው። አንዳንድ ወጣቶች ይህንን ተክል እንደ አደንዛዥ ዕፅነት የሚጠቀሙት ሲሆን ከብሩጋንዳ ጋር በጣም ሰለሚመሳሰል የሚያፈዘውንም መድሃኒት ከዚሁ ተክል ሊዘጋጅ ይችላል።

ስለ ዕጹ ድርጅቱ የሰራውን ዶኩመንታሪ ይመልከቱ።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s