የለንደን ኦሎምፒክስ ነገ በይፋ ይከፈታል

ኢትዮጲያውያን አትሌቶች ቢያንስ ሶስት የወርቅ ሜዳልያ እንደሚያስመዘገቡ እየተጠበቀ ነው።

30ኛው የበጋ ኦሎምፒክ ውድድር በነገው እለት በይፋ እንግሊዝ ዋና ከተማ በለንደን ይከፈታል። በአዘጋጅነት ከተመረጠችበት ግዜ ጀመሮ ላለፉት 7 አመታት የተለያዩ የከተማውን ውበት የሚያጎሉ ስራዎችን ጨምሮ አዲስ የኦሎምፒክ መንደር ያዘጋቸው ለንደን እንግዶቿን ተቀብላ ውድድሩን በየፋ ለማስጀመር ተዘጋጅታለች። ከ204 ኦሎምፒክ ቡድኖች የተወጣጡ ከ10000 በላይ አትሌቶችን በ26 የተለያዩ ስፖርቶች የሚወዳደሩ ሲሆን አገራችን ኢትዮጲያም 17 ሴቶችን እና 18 ወንዶችን ያቀፈ ቡድን ለውድድሩ አቅርባለች።

በ800፣ 1500፣ 3ሺ መሰናክል፣ 5ሺ፣ 10ሺ እና በማራቶን በወንዶችም በሴቶችም በ400 ደግሞ በወንዶች ብቻ የሚወዳደሩት ኢትዮጲያውያኑ ከአትሌቲክስ ውጪ ለመጀመሪያ ግዜ በሁለቱም ጾታ በውሃ ዋና ውድድር ላይ ይሳተፋሉ።

5ሺ ሜትር ፦ ጠንካራዎቹን ገለቴ ቡርቃ፣ መሰረት ደፋር እና ጥሩነሽ ዲባባን ያካተትው የሴቶቹ ቡድን በተለይ ከኬንያዎች የሚገጥመውን ፈተና ተቋቁሞ ውጤታማ ይሆናል ተብሎ ይገመታል። እንደሴቶቹ ያህል ጠንካራ ያልሆነው የወንዶቹ ቡድን ሃጎስ ገ/ህይወት እና የኔው አላምረውን በቀነኒሳ መሪነት ያሰልፋል። በዚህ ውድድር በተለይ ከእንግሊዛዊው ሞ ፋረህ እና ከአሜርካዊው በርናድ ላጋት ከፍተኛ ፈተና ሊገጥመው ይችላል።

10ሺ ሜትር ፦ አንጋፋዎቹን ቀነኒሳ በቀለ፣ ታሪኩ በቀለ እና ገ/እግዚአብሄር ገ/ማሪያምን ያካተተው የወንዶች ቡድን በዚህ ውድድር ሁሉንም ሜዳልያ የወስዳል ተብሎ ተጠብቋል። ጥሩነሽ ዲባባ እና ወርቅነሽ ኪዳኔን ያካተተው የሴቶቹ ቡድን እነ በላይነሽ ኦልጂራን የመሳሰሉ ተተኪ አትሊቶችን ይዞ ይቀርባል።

ማራቶን ፦ በሴቶች ውድድር ኬንያውያን በቅርብ ጊዜአት በተደጋጋሚ በማሸነፍ የበላይነታቸውን ቢይዙም በሮተርዳም ማራቶን ያሸነፈችው ቲኪ ገላና እና የዱባይ ማራቶን አሸናፊ አሰለፈች መርጊያ ጥሩ ተፎካካሪ ይሆናሉ ተብሎ ተገምቷል። በፈረንጆቹ 2012 ከተመዘገቡ 6 ፈጣን ሰአቶች ውስጥ 5ቱን ያስመዘገቡት ኢትዮጲያውያን በመሆናቸው ብርሃን ጌታሁን፣ ጌቱ ፈለቀ እና አየለ አብሽሮን የያዘው የኢትዮጵያ ቡድን ሁለቱን ሚዳሊያ ሊያገኙ ይችላሉ ተብሎ ይጠበቃል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s