ገና በ33 አመቱ የ30 ልጆች አባት?

አሜሪካን ውስጥ ቴኔሲ በሚባለው ክልል ነዋሪ የሆነው ዴዝሞን ሃቸት የ33 አመት ጎልማሳ ሲሆን ከ11 የተለያዩ ሴቶች የተወለዱ የ30 ልጆች አባትም ነው። ብዙ ተባዙ የሚለውን የመጽሃፍ ቅዱስ ጥቅስ እንደ ህይወቱ አላማ አርጎ የያዘ የሚመስለው ዴዝሞንት ሰሞኑን ዜና ላይ የወጣው ልጆቹን ማሳደጊያ ገንዘብ ከመንግስት እንዲሰጠው ጥያቄ በማቅረቡ ነበር። ዝቅተኛ ደሞዝ የሚያስገኝ ሰራ የሚሰራው ይህ ግለሰብ ምንም ያህል ደሞዙን ለልጆቹ መደጎሚያ ቢያከፋፍልም እንደማይበቃው ተረድቶ መንግስትን አቤት ብሎአል።

ታሪኩን በጣም አስገራሚ የሚያደርገው ደሞ እ.ኤ.አ በ2009 ዓ.ም ተመሳሳይ ጥያቄ አቅርቦ የነበረ መሆኑ ነው። በግዜው የልጆቹ ቁጥር 21 የነበረ ሲሆን ሌላ ልጅ ለመውለድ ምንም ሃሳብ እንደሌለው ተናግሮ ከመንግስት ትንሽ ድጎማ አግኝቶ ነበር። ነገር ግን ፍሬህ ይባረክ ተብሎ የተመረቀ የሚመስለው ዴዝሞን በሶስት አመት ውስጥ ተጨማሪ 9 ልጆች ወልዶ ሰዉን ጉድ አሰኝቷል። 30 ላይ ያቆማል ብሎ የሚወራረድ ካል ለማስያዝ ዝግጁ ነኝ!!

[Thisis50]

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s