ሁለቱን እግሮቹን በተፈጥሮ ችግር ያጣው አትሌት ለ400 ሜትር ኦሎምፒክ ግማሽ ፍጻሜ አለፈ

ደቡብ አፍሪካዊው ኦስካር ፒስቶሪየስ በተፈጥሮ ባጋጠመው የአጥንት አለማደግ ችግር ምክንያት በተወለደ በ11 ወሩ ከጉልበቱ በታች ያለውን የእግሩን ክፍል ለማጣት ተገዶ ነበር። በተሰራለት ሰው ሰራሽ ብረት እግር ታግዞ ህይወቱን መምራት የጀመረው ኦስካር በራግቢ፣ ቴኒስ እና ትግል የመሳሰሉ ስፖርቶች በትምህርት ቤት ደረጃ ይሳተፍ ነበር። ባጋጠመው ጉዳት ምክንያት ከራግቢ ጨዋታ ሲገለል ለስፖርት ካልው ትልቅ ፍቅር የተነሳ በሩጫ ውድድር መሳተፍ ጀመረ።

በአጭር ርቀት ውድድሮች ላይ መሳተፍ የጀመረው ደቡብ አፍሪካዊ ተመልካችን የሚያስደንቅ ውጤቶችን ማስመዝገብ የጀመረው ገና ከመነሻው ጀምሮ ነበር። እግር ሳይኖረው በመሮጡ የተለየ ትኩረት የሚደረግበት አትሌቱ በ1996 ዓ.ም እ.ኢ.አ በተካሂውደው የአቴንስ ኦሎምፒክ የአካል ጉዳተኞች ውድድር በመሳተፍ በ200 ሜትር ውድድር አሸናፊ ሊሆን ችሏል።

ቀስ በቀስ ሁለት እግር ካላቸው አትሌቶች ጋር የሚፎካከር ሰአቶች ማስመዝገብ የጀመረው ኦስካር ከነሱ ጋር ለመወዳደር በሚዘጋጅበት ሰአት ነበር ከአለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌደሬሽን አስገራሚ ዜና የተሰማው። ፌደሬሽኑ አደረግኩት ባለው ጥናት ኦስካር በብረት ታግዞ በመሮጡ የተለየ ጥቅም ስለሚያገኝ ከትክክለኛ ተወዳዳሪዎች ጋር መወዳደር እንደማይችል ወሰነ። ብዙዎችን ያስገረመውን ውሳኔ የተቃወመው ኦስካር ባቀረበው ይግባኝ የአለም የስፖርት ጉዳዮች ግልግል ፍርድ ቤት የአትሌቲክስ ፌደሬሽኑን ውሳኔ ውድቅ በማድረግ ማንኛውም ውድድር ላይ እንዲሳተፍ ተፈቅዶለታል።

በቤጂንግ ኦሎምፒክስ መካፈል ያልቻለው ኦስካር በለንደን 400 ሜትር የሚሮጥ ሲሆን ለግማሽ ፍጻሜ ውድድር እንዳለፈ ሲታወቅ ቀሪ ውድድሮችን በዛሬው እለት እና ነገ ያደርጋል። እንድ ነገር ለመስራት ነገሮች ከባድ መስለው ሲታዩ ይሄንን አትሌት ማስታወስ ነው እንግዴ። መልካም እድል ለኦስካር!! [NYTimes]

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s