በደማቅ ሁኔታ በቀጠለው የለንደን ኦሎምፒክስ ኢትዮጲያ በሁለት ወርቅ እና አንድ ነሃስ በሜዳልያ ሰንጠረዥ 22ኛ ደረጃ ይዛለች

የቀሩ ውድድሮችን ፕሮግራም ይዘናል።

በተለይ በዋና ውድድሮች በዛ ያሉ የአለም ሪከርዶች የተሰበሩበት የለንደን ኦሎምፒክስ በደመቀ ሁኔታ እንደቀጠለ ይገኛል። በወንዶች ዋና ውድድር በአጠቃላይ 19 ሜዳሊያዎችን በሶስት የተለያዩ ኦሎምፒኮች የሰብሰበው ማይክል ፌልፕስ በኦሎምፒክ ታሪክ ብዙ ሜዳልያ ባለቤትነትን ሪከርድ መያዝ የውድድሩ መነጋግሪያ የነበረ ሲሆን ወጣቷ ቻይናዊ ዋናተኛ ይኤ ሊን አስደናቂ ውጤት ካገኘች በኋላ የተነሳው የሃይል ማበረታቻ መድሃኒት ጉዳይም ብዙ ጥያቄዎችን የጫረ ዜና ነበር። ፌስቡክ እና ትዊተር የመሳሰሉ የማህበራዊ ሚዲያ ቴክኖሎጂዎች የኦሎምፒኩን ዜና እና የተለያዩ ሃሳቦችን በአለም አቀፍ ደረጃ በማንሸራሸር ለዝግጅቱ የተለየ ገጽታ ሰጥተውት ነበር። ኢትዮጲያውያንም ስለ ውድድሩ የተሰማቸውን ነገር በተለይ በፌስቡክ ሲገልጹ የነበረ ሲሆን በአጠቃላይ በ12 ሰአት ውስጥ ከ40000 በላይ ስለጥሩነሽ የሚያወሩ መልእክቶች  በፌስቡክ የተላለፉ ሲሆን ከቀነኒሳ ሽንፈት በኋላ ይህ ቁጥር ወደ 15000 ወርዶ ነበር።

የኢትዮጲያ ቡድን በለንደን ኦሎምፒክስ

የዋና ስፖርት ላልተስፋፋባቸው አገሮች በሚሰጥ የሎተሪ እድል ምክንያት በ50ሜትር ነጻ ዋና ውድድር ተሳታፊ የነበሩት ያኔት ሰዩም እና ሙሉአለም ተፈራ ጥሩ ተፎካካሪ ቢሆኑም ወደ ቀጣይ ዙር ማለፍ ተስኖአቸዋል። ቲኪ ጀላን ከፈተኛ ጽናት በሚጠይቀው የማራቶን ውድድር አዲስ የኦሎምፒክ ሪኮርድ በማስመዝገብ ጭምር የወርቅ ሜዳሊያ ያገኘች ሲሆን ማሬ እና አሰለፈች 23ኛ እና 42ኛ ሆነው አጠናቀዋል።

በሴቶች 10000ሜትር ውድድር ያላትን ውድድር የማንበብ ልምድ ተጠቅማ ዙሩን በማፍጠን መሪ ቡድን እንዲኖር ወርቅነሽ ኪዳኔ አስገራሚ የቡድን ሰራ ሰርታለች። ከመሪዎቹ ቡድን በጥሩ መንፈስ ስትሮጥ የነበረችው ጥሩነሽ ውድድሩ ሊያልቅ አንድ ዙርር አካባቢ ሲቀረው በመፈትለክ ውድድሩን በሰፊ ርቀት አሸንፋ በጉጉት የሚጠብቀውን የኢትዮጲያ ህዝብ አስደስታለች። በወንዶቹ ውድድር በአንጻሩ የኢትዮጲያ ቡድን እዚህ ግባ የሚባል የቡድን ስራ ሳይሰራ እና መኖሩ እንኳን ሳይታይ በእንግሊዛዊው ሞ ፋራህ እና አሚሪካዊው ጋለን ሩፕ ተበልጦ ታይቷል። ቀነኒሳ ለመፈትለክ የሚገባወን ቦታ ማመቻቸት እንዳይችል በአሜሪካዊው አትሌት ተየዞ የነበረ ሲሆን ልምዱን ተጠቅሞ ይህንን አለማመቻቸቱ የአቋም መውረድ እንደታየበት ያሳያል። ለአንድ አመት ገደማ ባጋጠመው ጉዳት ምክንያት የአቋም መቀነስ የታየበት ቀነኒሳ በጥሩ አቋም ላይ መሮጡን ብዙዎች ይጠራጠራሉ። በውድድሩ አጋማሽ አካባቢ ሁኔታዎችን በማጤን አሸንፎ መጨረስ የሚችል መስሎ ከተሰማው ታሪኩን ዙሩን እንዲያከርለት መጠየቅ ወይም የሚከብደው ከመሰለው እራሱ ዙሩን በማክረር ለታሪኩ ሁኔታዎችን ማመቻቸት እንደነበረበት ታይቷል። በ10000ሜትር ሁለቱም ውድድር ተተኪ አትሌቶች ላይ ብዙ መሰራት እንዳለበት ያሳየ ሆኖ አልፎአል።

በ3000ሜትር ዝላይ በወንዶች ሮባ ጋሪ እና መስፍን ናሆም ወደ መጨረሻ ዙር ያለፉ ሲሆን በሴቶቹ እሸቴ ዲሮ፣ ህይወት አያሌው እና ሶፊያ አሰፋም በመጨረሻ ዙር ውድድር ይሳተፋሉ። በ400ሜትር ተሳታፊ የነበረቅ በረከት ደስታ ማጣሪያውን ማለፍ ሳይችል ሲቀር በ1500ሜትር ከቀረቡ ሶስት ኢትዮጲያውያን መካከል መኮንን ገ/መድህን ብቻ ለቀጣዩ ዙር ማለፍ ችሏል።

የቀሩ ውድድሮች

አትሌቶች ፦ መኮንን ገ/መድህን
ውድድር ፦ 1500 ሜትር ወንዶች
ግማሽ ፍጻሜ – ሃምሌ 29 2004 ከምሽቱ 4:15
የመጨረሻ ውድድር – ነሃሴ 1 2004 ከምሽቱ 5:15

አትሌቶች ፦ ናሆም መስፍን፣ ሮባ ጋሪ
ውድድር ፦ 3000 ሜትር ዝላይ ወንዶች
የመጨረሻ ውድድር – ሃምሌ 29 2004 ከምሽቱ 4:25

አትሌቶች ፦ ሞሃመድ አማን
ውድድር ፦ 800 ሜትር ወንዶች
የመጀመሪያ ዙር – ሃምሌ 30 2004 ከቀኑ 6:50
ግማሽ ፍጻሜ – ነሃሴ 1 2004 ከምሽቱ 3:55
የመጨረሻ ውድድር – ነሃሴ 3 2004 ከምሽቱ 4፡00

አትሌቶች ፦ አበባ አረጋዊ፣ መስከረም አሰፋ፣ ገንዘቤ ዲባባ
ውድድር ፦ 1500 ሜትር ሴቶች
የመጀመሪያ ዙር – ሃምሌ 30 2004 ከቀኑ 7:45
ግማሽ ፍጻሜ – ነሃሴ 2 2004 ከምሽቱ 3:45
የመጨረሻ ውድድር – ነሃሴ 4 2004 ከምሽቱ 4፡55

አትሌቶች ፦ እሸቴ ዲሮ፣ ህይወት አያሌው እና ሶፊያ አሰፋ
ውድድር ፦ 3000 ሜትር ዝላይ ሴቶች
የመጨረሻ ውድድር – ሃምሌ 30 2004 ከምሽቱ 5:05

አትሌቶች ፦ ፋንቱ ሞጂሶ
ውድድር ፦ 800 ሜትር ሴቶች
የመጀመሪያ ዙር – ነሃሴ 2 2004 ከቀኑ 3:35
ግማሽ ፍጻሜ – ነሃሴ 3 2004 ከምሽቱ 3:30
የመጨረሻ ውድድር – ነሃሴ 5 2004 ከምሽቱ 4፡00

አትሌቶች ፦ መሰረት ደፋር፣ ገነት ያለው፣ ገለቴ ቡርቃ
ውድድር ፦ 5000 ሜትር ሴቶች
ግማሽ ፍጻሜ – ነሃሴ 1 2004 ከቀኑ 6:55
የመጨረሻ ውድድር – ነሃሴ 4 2004 ከምሽቱ 4:05

አትሌቶች ፦ ደጀን ገ/መስቀል፣ ሃጎስ ገ/ህይወት፣ የኔው አላምረው
ውድድር ፦ 5000 ሜትር ወንዶች
ግማሽ ፍጻሜ – ነሃሴ 2 2004 ከቀኑ 6:45
የመጨረሻ ውድድር – ነሃሴ 5 2004 ከምሽቱ 3:30

አትሌቶች ፦ አየለ አብሽሮ፣ ዲኖ ሰፈር፣ ጌቱ ፈለቀ
ውድድር ፦ ማራቶን ወንዶች
የመጨረሻ ውድድር – ነሃሴ 5 2004 ከቀኑ 7:00

Advertisements

1 Comment

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s