በሻርኮች ተከቦ የነበረ አውስትራሊያዊ በአደጋ ሰራተኞች እርዳታ ለጥቂት ተረፈ

ሁለት አውስትራሊያዊ አሳ አጥማጆች እስካሁን እንዴት እንደተፈጠረ ባልታወቀ ሁኔታ ወደ ውቅያኖስ ውስጥ ከወደቁ በኋላ ያልታሰበ ነገር ነበር ያጋጠማቸው። በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ በርካታ ሻርኮች ወደ እነሱ ካመሩ በኋላ ዙሪያቸውን በመክበብ ሊበሏቸው ማንዣበብ ጀመሩ። በአጋጣሚ በአካባቢ ያልፍ የነበረ የቴሌቭዥን ሄሊኮፕተር ሁኔታውን መቅረጽ እንደጀመረ አሳ አጥማጆቹም ለመንሳፈፍ እየታገሉ የአድኑን ልመናቸውን ተያያዙት። ሄሊኮፕተሩ ላይ የነበሩት ባለሙያዎች ምንም አይነት እርዳታ ማድረግ ባይችሉም ሁኔታውን ለአደጋ ግዜ ሰዎች በማሳወቅ እርዳታ እስኪደርስ ካሜራቸውን ደቅነው በጭንቀት መቅረጹን ቀጠሉ። የእርዳታ ጀልባ በፍጥነት ደርሶ ሁለቱን ሰዎች ከሻርኮቹ ማትረፍ ቢችሉም አንደኛው ሰውዬ ሆስፒታል እንደደረሰ ህይወቱ ማለፉ ታውቋል። የሞቱ መንስኤ እስካሁን ያልታወቀ ሲሆን ሁለተኛውም ሰው በአሁኑ ሰአት ሆስፒታል እንደሆነ ታውቋል። የተቀረጸውን ቪዲዮ ይመልከቱ። [CNN]

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s