ቡሄ (ሆያ ሆዬ)

በአሁኑ ሰአት አለማችንን እያዳረሰ ያለው አለማቀፋዊነት (globalization) እያዳከማቸው መጣ እንጂ በሃገራችን ኢትዮጲያ በዛ ያሉ የህጻናት ጨዋታዎች፣ ተረቶች እና ዘፈኖች አሉ። እነ ብይ፣ ቆርኪ፣ ጠጠር፣ እርርግጫ፣ ካሬ፣ ዲሞ፣ ወደም፣ አባሮሽ፣ ሱዚ የመሳሰሉ ጨምሮ ሌሊች ብዙ አዝናኝ ጨዋታዎች አሉ።። ከነዚህ ውስጥ አንዱና በወንዶች የሚዘመረው ሆያ ሆዬ ዘፈን እና አብሮት የሚከበረው የኦርቶዶክስ እምነት በአል ቡሄ ነው። በሃይማኖቱ የእየሱስ ክርስቶስን በታቦር ተራራ ላይ መለወጥ የሚዘከርበት ይህ ቀን በብርሃኑ አምሳያ ችቦ በማንደድ የሚከበር በአል ነው።

በአሉን ምክንያት በማድረግ የተጀመረው ስርአት ወንዶች ህጻናት ውስጥ ወርቶ በሆያ ሆዬ ሙዚቃ በሰፊው ይከበራል። በበዓሉ እለት በባህላዊው ገጽታው ወጣት ወንዶች ኩታቸውን አርገው በአካባቢያቸው ያሉ ቤቶች እየዞሩ በዘፈን በማሞገስ ሙልሙል ዳቦ እየተሰጣቸው ይበሉ ነበር። በአሁኑ ሰአት በከተሞች አለባብሱ የተተወ ቢሆንም ህጻናት ወንዶች በየቤቱ በመዞር ሆያ ሆዬ እያዜሙ ገንዘብ መቀበል የነሃሴ 12 መለያ ነው። ከገንዘብ ጋር በብዛት መተሳሰሩ የግጥሞችን ይዘት እና ለዛ እያደበዘዘው ቢመጣም በቅብብል የሚዘፈነው ዘፈን አሁንም መሰረቱን አለቀቀም።

ሆያ ሆዬ .. ሆ
ሆያ ሆዬ .. ሆ
እዛ ማዶ .. ሆ .. ጭስ ይጨሳል .. ሆ
አጋፋሪ .. ሆ .. ይደግሳል .. ሆ
ያቺን ድግስ .. ሆ .. ውጬ ውጬ .. ሆ
በድንክ አልጋ .. ሆ .. ተገልብጬ .. ሆ
ያቺ ድንክ አልጋ .. ሆ .. አመለኛ .. ሆ
ካላንድ ሰው .. ሆ .. አታስተኛ .. ሆ
ሆያ ሆዬ ጉዴ ጨዋታ ነው ልማዴ
ሆያ ሆዬ ጉዴ ጨዋታ ነው ልማዴ

የኔማ ጋሼ .. ሆ .. የሰጠኝ ሙክት .. ሆ
ከግንባሩ ላይ .. ሆ .. አለው ምልክት .. ሆ
መስከረም ጠባ .. ሆ .. እሱን ሳነክት .. ሆ
ሆያ ሆዬ ጉዴ ጨዋታ ነው ልማዴ

ስጦታ ከተሰጠ በኋላ ምርቃቱም

አውደአመት አመት .. ድገምና .. አመት .. ድገምና
የማምዬን ቤት .. ድገምና .. አመት .. ድገምና
ወርቅ ይፍሰስበት .. ድገምና .. አመት .. ድገምና
ያባብዬን ቤት .. ድገምና .. አመት .. ድገምና
ወርቅ ይፍሰስበት .. ድገምና .. አመት .. ድገምና

የዘንድሮ ህጻናት ካፌ ውስጥ ለተቀመጠ ሰው ሁሉ መጨፈር ጀምረው ነገሩን ማመሰቃቀላቸው ባይቀርም የችቦ ዝግጅቱ፣ አሻሻጡ እናም በጋራ ሆኖ ማብራቱ አሁንም ሞቅ እንዳለ እየቀጠለ ነው። በአሉን በማስመልከት አንድ ባህላዊ ሌላ ደሞ ዘመናዊ ሆና ቀልድ ጣል ያለባት ሆያ ሆዬ ልጋብዝ።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s