ሞሃመድ አማን በስዊዘርላንድ በተካሄደው የዳይመንድ ሊግ ውድድር አሸነፈ

በለንደኑ ኦሎምፒክ የአለምን ሪከርድ በመስበር ያሸነፈውን ኬንያዊ ቀድሞት ገብቷል

ሞሃመድ አማን

ኢትዮጲያውያን አትሌቶች እምብዛም በማይታወቁበት በመካከለኛ ርቀት አትሌቲክስ ውድድሮች ጥሩ ጥሩ አትሌቶች ብቅ እያሉ ነው። በፊት ዝነኛዋ ገለቴ ቡርቃ በዚህ ርቀቶች የምትታወቅ ሲሆን አሁን አሁን አበባ አረጋዊ እና ሞሃመድ አማን የመሳሰሉ ወጣት አትሌቶች ብቅ እያሉ ነው። መሃመድ በመጀመሪያ በተካፈለበት በለንደን ኦሎምፒክስ 800ሜትር ውድድር ማጣሪያዎችሁን በማለፍ ፍጻሜ ውድድር ማለፍ ችሎ ነበር። በውድድሩ ስድስተኛ ወጥቶ ሜዳሊያ ባያገናም የኢትዮጲያን እና የራሱን ሪከርድ አሻሽሎ ነበር ያጠናቀቀው።

ከኦሎምፒክስ በኋላ አሁን በተከፈተው የዳይመንድ ሊግ ውድድር በመሳተፍ ላይ ሲሆን በዙሪክ በተካሄደ የ800ሜትር ውድድር ላይ የአለም ሪከርድ ባለቤቱን ኬንያዊ ዴቪድ ሩሺዳን ቀድሞ በመግባት አሸናፊ ሆኗል። በዚህም ውድድር የራሱን እና የኢትዮጲያን ሪከርድ በማሻሻል ነው ያጠናቀቀው። በአሰላ ከተማ የተወለደው ሞሃመድ ገና የ18 አመት እድሜ ወጣት ሲሆን ከጥቂት አመታት በኋላ ችሎታው ሲዳብር በርቀቱ አስፈሪ ተፎካካሪ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። የውድድሩን ቪዲዮ ከታች ይመልከቱ።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s