እንቁጣጣሽ – እንኳን አደረሳችሁ

2004 አመትን ተሰናብተን ዛሬ አዲሱን አመት ተቀብለናል። በአለም ላይ በአገር አቀፍ ደረጃ የጁሊያን ካላንደርን የምትጠቀመው ኢትዮጲያ እንቁጣጣሽን ከሌሎች በአሎች ደመቅ ባለ መልኩ ታከብራለች። በመስከረም ክረምቱ አልቆ፣ መስኮች በቢጫ አደይ አበባ ተውበው የምንቀበለው አዲስ አመት ቀጥሎ ከሚመጣው የአዲስ የትምህርት ዘመን ጋር ተያይዞ ብዙ እንቅስቃሴ የሚበዛበት በአል ነው። በዋዜማው እና በእለቱ ሴቶች ህጻናት አበባየሆሽ እያዜሙ በአሉን የሚያደምቁት ሲሆን ወንዶች ህጻናት አዲሱ አመት መልካም እንዲሆን የሚመኙ ቀለም የበዛባቸው ስዕሎች በየቤቱ ይሰጣሉ።

ሆ ብለን መጣን ሆ ብለን … እማማ አሉ ብለን
ሆ ብለን መጣን ሆ ብለን  … አባባ አሉ ብለን
አበባየሆሽ … ለምለም … አበባየሆሽ … ለምለም
ባልንጀሮቼ … ለምለም … ግቡ በተራ … ለምለም
እንጨት ሰብሬ … ለምለም … ቤት እስክሰራ … ለምለም
እንኳን ቤትና … ለምለም … የለኝም አጥር … ለምለም
እደጅ አድራለሁ … ለምለም … ኮከብ ስቆጥር … ለምለም
ኮኮብ ቆጥሬ … ለምለም … ስገባ ቤቴ … ለምለም
ትቆጣኛለች … ለምለም … የእንጀራ እናቴ … ለምለም
አደይ የብር ሙዳይ ኮለል በይ
አደይ የብር ሙዳይ ኮለል በይ

እቴ አበባሽ እቴ አበባዬ … አዬ እቴ አበባዬ
እቴ አበባሽ ስትለኝ ከርማ … አዬ እቴ አበባዬ
ጥላኝ ሄደች በሃምሌ ጭለማ … አዬ እቴ አበባዬ
እኔስ መጣሁ ጨለማ ፈክቶ … አዬ እቴ አበባዬ
ደስ ብሎኛል መስከረም ጠብቶ … አዬ እቴ አበባዬ

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s