ከባንክ ተዘርፎ በኤግዚቢትነት የቆየ ገንዘብ የሚወስደው ስለጠፋ ለዘራፊው ሊመለስ ነው

Ethiopian currency notes

ከ20 አመት በፊት ኦስትሪያ ውስጥ ኦቶ ኒውማን የተባለ የባንክ ቅርንጫፍ ሃላፊ ዝርፊያ የተካሄደ በማስመሰል 240 ሺህ የአሜሪካን ዶላር እና ብዙ ወርቆችን ከባንኩ ወደ ኪሱ ያስገባና ተዘረፈን ብሎ ለፖሊስ ያመለክታል። ፖሊስ በምርመራ ዝርፊያው የሃሰት መሆኑን እና እራሱ እንደወሰደው በማስረጃ አረጋግጦ ሰውየው የሶስት አመት እስር ተፈርዶበት ወደ ዘብጥያ  እጁ ላይ የቀረው ገንዘብ እና ወርቅ ደግሞ ወደ ኤግዚቢት ይገባል።

ከፍርዱ በኋላ ፖሊስ እግዚቢት ያለውን ንብረት ለባንኩ ለመመለስ ቢሞክርም ባንኩ ለደህንነቱ ከኢንሹራንስ የገዛው ዋስትና በመኖሩ የተዘረፈውን ያህል ንብረት ከኢንሹራንሱ ስለተቀበለ ኤግዚቢት ያለውን ንብረት እንደማይፈልግ ያስታውቃል። በኋላም የኤግዚቢቱን ወርቆች እና ገንዘብ ፖሊስ ሁለተኛው ተጎጂ ለሆነው ለኢንሹራንሱ ያስረክባል። ኢንሹራንሱም ለባንኩ የከፈለውን ገንዘብ ለማስመለስ ወርቁን ለገበያ ያወጣዋል። የወርቅ ዋጋ በግዜው ንሮ የነበረ በመሆኑ ኢንሹራንሱ ከወርቁ ሽያጭ ያገኘው ገቢ እና በእጁ የሚገኘው ጥሬ ገንዘብ ሲደመሩ ለባንኩ የከፈለውን ሙሉ ገንዘብ ያካክስ እና 80 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ትርፍ ያገኛል። ከዛም ትርፉን ገንዘብ መውሰድ ስለማይችል ይህንን ገንዘብ ለፖሊስ መልሶ ያስረክባል።

ገንዘቡ በፖሊስ ስር ለረጅም ግዜ ከቆየ በኋላ የሃገሪቷ ፍትህ ሚኒስቴር ጉዳዩን ሲመለከተው ባንኩም ሆነ ኢንሹራንሱም በስርቆቱ የተጎዱ ባለመሆኑ፣ ሰውየውም የተጣለበትን እስር ቅጣት መጨረሱ እና ገንዘቡን የሚወስድ ሌላ አካል አለመኖር በማየት ለዘራፊው እንዲሰጠው ወስኗል።

ዘራፊው ከ20 አመት በኋላ የስራውን ፍሬ ያጣጥማል ማለት ነው። [Gawker]

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s