በኢትዮጲያ ውስጥ ያለ አሰቃቂ ጎጂ ባህል በለውጥ ጎዳና

በደቡብ ኢትዮጲያ ውስጥ የሚገኝ ‘ካራ’ የሚባል ጎሳ ውስጥ የተወለደ ህጻን የላይኛው ጥርስ ከስረኛው ጥርስ ቀድሞ ከወጣ በአካባቢው የመጥፎ መንፈስ የሚያመጣ የተረገመ ልጅ ነው ብለው ያምናሉ። የጎሳው አባላት ህጻኑን “ሚንጊ” ብሎ በመሰየም አካባቢያቸውን ከመጥፎ መንፈስ ለመጠበቅ በሚል ህጻኑን ልጅ ይገድሉታል። ይህ ጎጂ ባህል ከካራዎች በተጨማሪ ‘ባና’ እና ‘ሃመር’ የተሰኙ ጎሳዎችም ውስጥ ይፈጸም እንደነበር ታውቋል።

የክልሉ መንግስት ስለ ሁኔታው መረጃዎችን ከሰበሰበ በኋላ ግን ሚንጊዎችን የሚገድሉ ሰዎችን ወደ ህግ በማቅረብ ቅጣት እንዲወሰንባቸው እያደረገ ይገኛል። በአካባቢው ያሉ የክርስትና እምነት ተከታይ የጎሳ አባላትም ሊገደሉ የነበሩ ሚንጊዎችን በማዳን በአካባቢያቸው ያለ ማሳደጊያ ውስጥ እንዲያድጉ እያደረጉ ይገኛሉ። እነዚህ እርምጃዎች የተወሰነ ለውጥ ማምጣት ቢችሉም የጎሳዎቹን አስተሳሰብ በማስቀየር የሚንጊዎችን ግድያ ሙሉ በሙሉ ማስቆም አልተቻለም።

ከትዳር ውጪ ልጆችን መውለድ በአካባቢው የተለመደ ቢሆንም ትዳር ሳይዙ ግን የሚፈጠር እርግዝና እና ልጅ በአካባቢው የመጥፎ መንፈስ ያመጣሉ ተብሎ ስለሚታሰብ የሚንጊዎች እጣ ነው የሚጠብቃቸው። ስለ ባህሉ አመጣጥ ብዙ የሚታወቅ ነገር ባይኖርም ለጎሳቸው የሚገባቸውን ነገር የማያዋጡ ሸክም ይሆናሉ ብለው የሚገምቷቸውን ሰዎች የሚያስወግዱበት መንገድ አርገው እንደሚቆጥሩ ይገመታል። ይህ ባህል በተለይ ለጎሳዎቹ መሪዎች የሚንጊዎቹ አብረዋቸው መኖር ድርቅ እና ረሃብ በአካባቢው ህዝብ ላይ ያመጣል ብለው ያስባሉ።

ሁኔታውን ለማየት በአካባቢው የተገኙ ጋዜጠኞች በቦታው የሚገኝ እስር ቤት ውስጥ አንዲት እድሜዋ በአስራዎቹ ቤት የሚሆን እስረኝ ያነጋግራሉ። እስረኛዋ እናት ሚንጊ ልጇ ከተገደለ በኋላ ፖሊሶች በአካባቢው ተገኝተው ማን ድርጊቱን እንደፈጸመ ሲጠይቁ እራሷን በማጋለጥ ወደ እስር ቤት መግባቷን ተናግራለች። ብዙዎች እናቶች የራሳቸውን ልጅ እንደማይገድሉ የታወቀ ቢሆንም የአካባቢዋን ባህል ለመጠበቅ ስትል ጥፋተኛ ነኝ እንዳለች ይገምታሉ። እሷ ግን በቃሏ በመጽናት ሌሎቹ የሚያወሩት ሃሰት እንደሆነ እና ልጁን እንደምትወደው ነገር ግን ባህላቸው ስለሆነ ራሷ ህይወቱን እንዳሳጣች ትናገራለች።

የጎሳው ተወላጅ የሆነው አቶ ሾማ ዶሬ በልጅነቱ ነበር ጎሳውን ትቶ ወደ ጂንካ በመምጣት የቀለም ትምህርት መከታተል የጀመረው። የባህሉን አስከፊነት ተረድቶ አንድ ነገር ለማድረግ በማሰብ ወደ ትውልድ ቦታው በመመለስ ከጎሳው ወጥተው መኖር የጀመሩ በርካታ ወጣቶችን አሰባስቦ ግድያው እንዲዎም ከጎሳው መሪዎች ጋር ውይይት አድርጎ ነበር። በውይይቱ ላይም ህጻናቱን ሳይገድሉ ለሱ እንዲያስረክቡት እና ከአካባቢው ስለሚርቁ ጎሳው ደህና እንደሚሆን መሪዎቹን ካሳመነ በኋላ እርዳታ በማሰባሰብ ለህጻናቱ ማሳደጊያ ድርጅት አቋቋመ።

ቀስ በቀስ ብዙ እርዳታ እያገኘ የመጣው የማሳደጊያ ተቋም በአሁኑ ሰአት 30 ሚንጊ ህጻናትን እያሳደገ ሲሆን ህጻናቱን ከአካባቢው አስተዳደር በስተቀር ሌሎች ሰዎች እንዲያገኛቸው አይፈቀድም። ይህ ህጻናቱን ከሌላ ተጸእኖ ለመከላከል የተደረገ እንደሆነ ያስታወቀው የማደጎው አስተዳዳሪ አቶ አርዮ ዶራ ህጻናቱ ሲያድጉ የወደፊቱ የጎሳው መሪዎች እንደሚሆኑ እና ጎጂ ባህሉን እንደሚያስቀሩ ተናግሯል።

ማደጎ ጣቢያው ህጻናቱን እየረዳ ቢሆንም ጎሳው ሰፊ ቦታ ሸፍኖ በሶስት መንደሮች ስለሚገኝ የተወለዱ ህጻናትን ደርሶ ማትረፍ አስቸጋሪ እንደሆነ ታውቋል። ከሶስቱ መንደሮች ውስጥ ስልክ በአንዱ ቦታ የሚገኝ ሲሆን ሌሎቹ መንደሮች ውስጥ የተወለደ ሚንጊ ካለ የአካባቢው ሰዎች ወደ ዋናው መንደር የአንድ ሰአት የእግር ጉዞ አድርገው ማደጎው ወዳለበት ጂንካ ስልክ ተደውሎ መኪና እስኪመጣ ግዜ ስለሚፈጅ ህጻናቱን ሁልግዜ ማትረፍ አይቻልም።

ከማደጎው በተጨማሪ ሌሎችም ድርጅቶች ይህንን ጎጂ ባህል ለማስቀረት እየሞከሩ ነው። ከነዚህ ውስጥ አንዱ አንድሪያስ ኮሱቤክ የተባለ ጀርመናዊ ሚሽነሪ የሚመራው የህክምና ቡድን ነው። ጎሳዎቹን በህክምና በማገዝ የጀመረው ቡድኑ የጎሳው መሪዎች በጭካኔ ሳይሆን ህዝባቸው እንዳይጠፋ ባላቸው ፍርሃት ድርጊቱን እንደሚደግፉ ተናግሮአል። ከሚንጊ ግድያ የሚበልጡ ህጻናት በትንንሽ በሽታዎች እንደሚሞቱ የተናገረው ይህ ጀርመናዊ ለአካባቢው የተቀናጀ እገዛ እንደሚያስፈልግ ተናግሮአል። [CNN]

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s