የስፖርት ጋዜጠኛ ደምሴ ዳምጤ ከዚህ አለም በሞት ተለየ

አንጋፋው የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የስፖርት ጋዜጠኛ ደምሴ ዳምጤ ባደረበት ህመም በህክምና ሲረዳ ቆይቶ በትላንትናው እለት ከዚህ አለም በሞት ተለየ።

ጋዜጠኛ ደምሴ ዳምጤ ላለፉት ሶስት ዓመታት በህመም ምክንያት ከሚወደው ሙያ ተለይቶ ህክምናውን በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ሲከታተል ቆይቷል። ከጥቂት አመታት በፊት ያጋጠመውን የአይን ህመም በታይላንድ ባንኮክ ታክሞ የነበረ ሲሆን በቅርቡ ደግሞ በህንድ ሀገር የኩላሊት ህክምና ተደርጎለት ተመልሷል። ከተመለሰም በኋላ ህመሙ ሙሉ በሙሉ ያልዳነ በመሆኑ ላለፉት ሁለት ወራት አዲስ አበባ በሚገኘው የፖሊስ ሆስፒታል ህክምናውን ሲከታተል ቆይቶ ጥቅምት 26 ቀን 2005 ከቀኑ በ9 ሰዓት ህይወቱ አልፏል።

ጋዜጠኛ ደምሴ ተወልዶ ያደገው ድሬደዋ ሲሆን ከ33 ዓመት በፊት በኢትዮጵያ ሬድዮ ከመቀጠሩ በፊት የስፖርት ፊሪላንስ ጋዜጠኛ ሆኖ ከትውልድ ስፍራው ይሰራ ነበር። በኢትዮጲያ የስፖርት ጋዜጠኝነት የማይዘነጋ አሻራ ጥሎ ያለፈው ደምሴ ዳምጤ በተለይ በሃገራችን በተዘጋጀው በ15ኛው የምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ የእግር ኳስ ውድድር የቀጥታ ዘገባው ሁሌም የሚታወስ ይሆናል። ኢትዮጲያ እግር ኳስ ቡድን ከዚምባብዌ አቻው ጋር ለዋንጫ በተፋለመበት በዚህ ጨዋታ የደምሴ ስሜታዊ ዘገባዎች መቼም አይረሱም።

ለኢትዮጵያ ስፖርት እድገት ደከመኝ ሳይል የሰራና በዚህም በህዝብ ዘንድ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያተረፈው ጋዜጠኛ ደምሴ ዳምጤ ባለትዳርና የሶስት ሴት ልጆች አባት ነበር።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s