ቡና ከ70 አመት በኋላ ከአለም ላይ ሊጠፋ እንደሚችል ተመራማሪዎች አሳወቁ

ተቀማጭነቱ በእንግሊዝ የሆነው ኬው የእጽዋት ማሳደጊያ እና ምርምር ጣቢያ ውስጥ የሚገኙ ተመራማሪዎች በኢትዮጲያ ከሚገኙ አቻዎቻቸው ጋር በህብረት ባደረጉት ምርምር በአለም የአየር ጸባይ ለውጥ ምክንያት በኢትዮጲያ የሚበቅለው አረቢካ ቡና ከ70 አመት በኋላ ሊጠፋ እንደሚችል ተናግረዋል። ይህ የብዙ ቡና ዝርያዎች ምንጭ የሆነው የቡና አይነት መጥፋት ደሞ ቀስ በቀስ ሌሎቹም ዝርያዎች እንዲጠፉ እንደሚያደርግ ተናግረዋል። በአየር ለውጥ ምክንያት ሊከሰት የሚችለው ይህ ችግር በአለም አንደኛ ተወዳጅ የሆነውን ቡናን ከገበያ ሊያጠፋው እንደሚችል እና ከነዳጅ ዘይት ቀጥሎ በአለም ሁለተኛው የንግድ መሰረት የሆነው ቡና ንግድ ላይ የተመሰረቱ እኮኖሚዎችን እንደሚጎዳ ታውቋል።

የቡናን ተፈጥሮአዊ አስተዳደግ ከአለም የአየር ትንበያ ጋር ባጣመረው በዚህ ምርምር ተክሉ አሁን በሚበቅልባቸው ቦታዎች ላይ እንኳን ጥሩ አየር ቢኖር የምርት መጠኑ በ65% የሚቀንስ ሲሆን መጥፎ አጋጣሚዎች ከበዙ ደግሞ የምርት መጠኑ 99.7% በመቀነስ ሊጠፋ እንደሚችል ተንብየዋል። አሁን በማይበቅልባቸው ነገር ግን ለእድገቱ ተስማሚ የሚባሉ ቦታዎች ቢተከል ደግሞ ከ70 አመት በኋላ ጥሩ አየር ካገኘ 38% ካላገኘ ደግሞ 90% እንደሚቀንስ ተንብየዋል። የትንበያቸውን ትክክለኛነት ለመገመት እ.ኤ.አ በ1941 በደቡብ ሱዳን ውስጥ በሚገኝ ደን ውስጥ ካለ የአረቢካ ቡና የተወሰደ መረጃ ላይ በኮምፒውተር የታገዘ ትንበያውን ያካሄዱ ሲሆን በቦታው ያለው ቡና እ.ኤ.አ በ2020 እንደሚጠፋ ግምት አስቀምጠው ነበር። እናም ክወራት በፊት ቦታው ላይ ከ70 አመት በኋላ ተመልሰው የሰበሰቡት መረጃ እንደሚያሳየው በቦታው ያለው ቡና መጥፎ ሁኔታ ላይ ያለ እና እንደ ትንበያው በጥቂት አመታት ውስጥ እንደሚጠፋ ተናግረዋል።

በኢትዮጲያ በሰፊው የሚታየው የደን ጭፍጨፋ የአየር ለውጡን በማዛባት መጥፊያውን እንደሚያቃርብ የተነብዩት ሳይንቲስቶቹ ይህንን ዝርያ ለማቆየት በዘረመል ምህንድስና የታገዘ ጥበቃ እንደሚያስፈልግ አሳውቀዋል። [Laboratory Equipment, ፎቶ – cbcnews]

Advertisements

1 Comment

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s