የአለማችን ውድ ምግቦች

1. ሳፍሮን ፦ በተመሳሳይ ስም ከሚጠራ አበባ የሚገኘው ይህ ቅመም ተወዳጅ ጣዕም ያለው ሲሆን ዋጋውን ያስወደደው ግማሽ ኪሎ የሚመዝነውን ቅመም ለማዘጋጀት የሚያስፈልገው አበባ አንድ የእግር ኳስ ሜዳ ሙሉ የሚሸፍን መሆኑ ነው። እንደ አበባው ጥራት የቅመሙ ዋጋ የሚለያይ ሲሆን አንድ ኪሎ ሳፍሮን እስከ 11000 ዶላር ያወጣል። ዋጋውን ለማነጻጸር ያህል ኢትዮጲያ ለውጪ ገበያ የምታቀርበው አንደኛ ደረጃ የይርጋጨፌ ቡና በኪሎ ዋጋው 3 ዶላር አካባቢ ነው።

Iran_saffron_threads

2. ካቪያር ፦ በድሮ ግዜ በምስራቅ አውሮፓ የንጉሳዊ ቤተሰቦች ብቻ የሚመገቡት ካቪያር ልዩ የሆነ ከአሳ እንቁላል የሚዘጋጅ ምግብ ነው። ዋጋው እንደ አሳው ዝርያ የሚለያየው ካቪያር በኪሎ እስከ 5000 የአሜሪካን ዶላር ድረስ ይሸጣል።

ካቪያር

3. ነጭ እንጉዳይ ፦ በሰሜን ጣልያን የሚበቅለው የዚህ እንጉዳይ ዝርያ ዋጋ በኪሎ እስከ 4000 ዶላር ያወጣል። በብዛት ስለማይገኝ ዋጋው የተወደደው ይህ እንጉዳይ በአንድ ወቅት ለጨረታ ቀርቦ በኪሎ 200,000 ዶላር ገዢ አግኝቶ ነበር።

ነጭ እንጉዳይ

4. ዋግዩ ስጋ ፦ ይህ ስጋ ጃፓን ውስጥ የሚገኙ እጅግ ጥራት ያለው ሳር የሚቀለቡ ከብቶች ውጤት ነው። ከብቶቹ ከሚደረግላቸው የምግብ እና የንፅህና ጥንቃቄ በተጨማሪ የስጋውን ጥራት ለመጠበቅ ማሳጅም ይደረጋሉ። በመጨረሻም ስጋቸው ለገበያ ቀርቦ በኪሎ እስከ 500 ዶላር ይሸጣል።

wagyu

5. ማካዴሚያ ለውዝ ፦ ይህ የአለማችን ውዱ እና ለመብቀል 7 አመት የሚፈጅበት ለውዝ ነው። ከምግብ ውጪ ለተለያዩ የቆዳ ቅባቶች ለማዘጋጀት የሚውለው ማካዴሚያ በኪሎ እስከ 30 የአሜሪካ ዶላር ይፈጃል።

ማካዴሚያ ለውዝ

ማካዴሚያ ለውዝ

6. በርክሻየር ሳንድዊች ፦ በእንግሊዟ በርክሻየር ከተማ ውስጥ የሚገኝ ፕላቲኒየም የተሰኘ ክለብ ውስጥ የሚዘጋጀው ሳንድዎች በልዩ ሁኔታ ከተዘጋጀ ሃም፣ የዶሮ ስጋ፣ እንቁላል፣ ቲማቲም እና በተራ ቁጥር 3 የተጠቀሰው ነጭ እንጉዳይ ነው የሚሰራው። ዋጋው 200 ዶላር ብቻ

በርክሻየር ሳንድዊች

በርክሻየር ሳንድዊች

7. ሉዊስ 13 ፒዛ ፦ በጣልያኖች የሚዘወተረው እና በአለም ላይ የሚያሳውቃቸው ፒዛ በአብዛኞቹ የአለማችን ከተሞች ተዳርሶ ተወዳጅነት ያገኘ ምግብ ነው። የሉዊስ 13 ፒዛ ለየት የሚያረገው ከካቪያር፣ ሎብስተር አሳ፣ 8 አይነት አይብ እና የተለየ የአውስትራሊያ ጨው መዘጋጀቱ እና በ12000 ዶላር መሸጡ ነው።

ሉዊስ 13

8. ወርቃማ ኬክ ፦ አይስ ክሬም፣ ቸኮሌት፣ የተለያዩ ፍራፍሬዎች ይዞ ከላዩ ላይ 23 ካራት ወርቃማ ሽፋን ጋር የሚቀርበው ይህ ኬክ በ1000 ዶላር በኒውዮርክ አሜሪካ ማጣጣም ይችላሉ።

ወርቃማ ኬክ

9. ላ ቦኖቴ ድንች ፦ ድንችም እዚህ ዝርዝር ውስጥ መግባቱ የሚያስገርም ቢመስልም ይህ የአለማችን ምርጡ ድንች እንደሆነ ይነገርለታል። ፈረንሳይ ውስጥ በምትገኝ ደሴት ላይ ከባህር አቅራቢያ ተመርቶ በኪሎ 650 ዶላር ለገበያ ይቀርባል።

la-bonnotte

ላ ቦኖቴ ድንች

[binscorner]

Advertisements

4 Comments

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s