በአንድ ጥንታዊ የቀን መቁጠሪያ ምክንያት አንዳንዶች አለም ትጠፋ ይሆን ብለው እየሰጉ ነው

mayan calendar

የማያ ቀን መቁጠሪያ

ከሶስተኛው ክፍለዘመን ጀምሮ ለስድስት መቶ አመታት የቆየ ስልጣኔ የነበራቸው የማያ ህዝቦች የላቀ የስነከዋክብት እውቀት እንደነበራቸው ይታመናል። ይህንን እውቀት በመጠቀም የቀመሩት የቀን መቁጠሪያ (ካላንደር) እ.አ.አ ዲሴምበር 21 2012 በኋላ መቁጠር ያቆማል። በዛን እለት ማቆም ብቻ ሳይሆን ማያዎች በእለቱ የጸሃይ እና የሌሎች የህዋ አካላት አቀማመጥ ምክንያት በሚነሳ የተፈጥሮ አደጋ አለም ትጠፋለች የሚል ትንበያም አላቸው። እናም ከቀኑ መቃረብ ጋር ተያይዞ ብዙዎች ፍርሃት ውስጥ የገቡ ሲሆን አንዳንዶች ከመጥፋታችን በፊት ማድረግ ይገባናል የሚሏቸውን ነገሮች ለመፈጸም እየተሯሯጡ ነው። ያፈሩትን ንብረት ሸጠው ቤተክርስቲያን የከተቱ፣ ቤተሰባቸውን መደበቂያ ጉድጓድ ቆፍረው ምግብ አከማችተው ቀኑን የሚጠብቁ እና ከተፈጥሮ ቀድመው የራሳቸውንም የቤተሰቦቻቸውንም ህይወት ለማጥፋት የሞከሩ ሰዎች እንዳሉ እየተሰማ ነው።

ይህ የአለም መጥፊያ የበለጠ አስፈሪ ያደረገው በማያ ቀን መቁጠሪያ ብቻ ሳይሆን በሌሎችም ትንበያዎች መደገፉ ነው። ከነዚህ ውስጥ መጽሃፍ ቅዱስን ፣ የኖስትራዳመስን ጽሁፎች እና በ16ኛው ክ/ዘመን በእንግሊዝ ነዋሪ የነበረች ሺፕተን የተባለች ፈላስፋ ትንበያዎች መሰረት በማድረግ የአለም መጨረሻ ከ2012 እንደማያልፍ ብዙዎች እየተናገሩ ነው። ሁለቱን የአለም ጦርነቶች በደንብ ተንብያለች የምትባለው ሺፕተን ለምሳሌ ስለ አለም መጥፊያ ስትናገር “ሃሳቦች በአለማችን ላይ በሰከንዶች ልዩነት የሚጓዙበት ግዜ የመጣ ግዜ የአለም ህዝብ ግማሹ ይጠፋል” ነበር ያለችው። ብዙዎች ኢንተኔት በሰከንዶች ልዩነት ሃሳብን ከአንድ የአለማችን ጥግ ወደ ሌላኛው ማጓጓዝ መቻሉ የዚህ ትንቢት አካል አርገው ይቆጥሩታል።

በተቃራኒው የአሜሪካ የህዋ ሳይንስ ምርምር ጣቢያ (ናሳ) የቀን መቁጠሪያው ማለቁ ልክ በአሁኑ ግዜ እንደምንጠቀመው መቁጠሪያ የአመት መጨረሻ ጷግሜ 5 አይነት እንደሆነ እና መስከረም 1 ብሎ አዲስ ዘመን እንደሚጀመር ይፋ አርጎአል። ነገር ግን በቅርቡ ስለሁኔታው የተሰበሰበ መረጃ እንደሚያሳየው ከ10 ሰዎች ውስጥ 1 ሰው የአለም መጥፊያ እ.ኤ.አ በ2012 እንደሚሆን ያምናሉ። እርሶስ ምን ይላሉ? [Huffingtonpost]

Advertisements

4 Comments

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s