የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዳጎስ ያለ ገንዘብ

uefa-champions-league-logo

በ32 የአውሮፓ ክለቦች መካከል በየአመቱ የሚካሄደው እና አንዳንዶች የአለማችን ተወዳጁ የእግርኳስ ውድድር ብለው የሚጠሩት ሻምፒዮንስ ሊግ የዘንድሮ አመት ወደ ሩብ ፍጻሜ የሚያስኬዱ ምድቦች ይፋ ሆኗል። ዘጠኝ ግዜ ውድድሩን ያሸነፈው ሪያል ማድሪድ ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር የተደለደሉበት ጨዋታ ከወዲሁ ማነጋገር የጀመረ ሲሆን ባርሴሎና ከኤሲ ሚላን እና አርሴናል ከባየር ሙኒክ የሚያደርጉት ጨዋታም የዘንድሮውን ውድድር በተመልካቾች እና በተጫዋቾቹ በጉጉት እንዲጠበቅ አድርጎታል። የክለቦቹ ባለቤቶች እና ሃላፊዎች ግን ከጨዋታው በተጨማሪ የሚያጓጓቸው ክለቦቹ በውድድሩ የሚያገኙት ዳጎስ ያለ ክፍያ ነው።

በመጀመሪያ ሁሉም 32 ክለቦች በውድድሩ ተሳታፊ በመሆናቸው እያንዳዳቸው 11.4 ሚሊዮን ዶላር የሚከፈላቸው ሲሆን በመጀመሪያው ዙር በሚያካሂዱት 6 ጨዋታ ካሸነፉ 1.3 ሚሊዮን ዶላር እና አቻ ከወጡ 650ሺህ ዶላር ከውድድሩ አዘጋጅ በሽልማት መልክ ያገኛሉ። ከዚህ በተጨማሪ ከታዳሚ እና ከቴሌቭዥን ስርጭት የሚያገኙት ገንዘብ ገቢያቸውን ያሳድገዋል። ለምሳሌ ማንቸስተር ዩናይትድ በአምናው ውድድር የመጀመሪያው ዙር ቢሰናበትም በአንድ ጨዋታ ከቴሌቭዥን ስርጭት እና ከተመልካች የሚያገኘው 5 ሚሊዮን ዶላር ታክሎበት በውድድሩ 45.6 ሚሊዮን ዶላር አግኝቶ ነበር።

የአምናው ባለዋንጫ የእንግሊዙ ቼልሲ ለፍጻሜ እስኪደርስ 32 ሚሊዮን ዶላር ያገኘ ሲሆን አሸናፊ በመሆኑ ተጨማሪ 32 ሚሊዮን ዶላር አግኝቶ በውድድሩ ያገኘውን የሽልማት መጠን ወደ 90 ሚሊዮን ዶላር ደርሶ ነበር። እግር ኳስ ለብዙዎች ተወዳጁ ጨዋታ ቢሆንም የሚንቀሳቀሰው ገንዘብ ሲታይ ከስፖርትነቱ አልፎ ትልቅ የንግድ መስክም ነው። [goal.com]

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s