ተንቀሳቃሽ ስልክ 40ኛ አመቱን አከበረ

የሞቶሮላ እና ኖኪያ የመጀመሪያው ተንቀሳቃሽ ስልኮች

የሞቶሮላ እና ኖኪያ የመጀመሪያው ተንቀሳቃሽ ስልኮች

በመጋቢት 25 1965 ዓ.ም ሞቶሮላ ድርጅት ውስጥ የሚሰራው ማርቲን ኩፐር ጋዜጠኞችን ሰብስቦ በሬድዮ ሞገድ የሚሰራ ስልክ በመጠቀም የመጀመሪያውን ጥሪ በማድረግ የተንቀሳቃሽ ስልክ ታሪክ ሀ ተብሎ ተጀመረ። ከወራት በኋላ የፈጠራ ባለቤትነት ማረጋገጫ በማግኘት የ’ተንቀሳቃሽ ስልክ አባት’ የሚል መጠሪያ አግኝቷል ማርቲን። የተንቀሳቃሽ ስልክ ሃሳብ የመነጨው ከማርቲን ጋዜጣዊ መግለጫ አስርት አመታት ቀድሞ ቢሆንም ቴክኖሎጂው አድርጎ ለህዝብ ገበያ የቀረበው በ1975 ዓ.ም ሲሆን ዋጋውም በጊዜው 4ሺ የአሜሪካን ዶላር ነበር።

ከጥቂት አመታት በኋላ የፊንላንዱ ኖኪያ ሁለተኛ የተንቀሳቃሽ ስልክ አምራች በመሆን መጠናቸውም አንቴናቸውም አነስ ያሉ ከድምጽ ውጪ ሌሎች መረጃዎችን ማስተላለፍ የሚያስችል ጂኤስኤም (GSM) ቴክኖሎጂን ያላቸው ስልኮችን ለገበያ አቀረበ። ቀስ በቀስ የጥሪ ሙዚቃ፣ አጫጭር መልክት የሚያስተላልፉ ስልኮች ብዛት ባላቸው አምራቾች እየተመረቱ ለገበያ መቅረብ እና ቴክኖሎጂውም በፍጥነት ማደጉን ተያያዘው።

iphone-5-vs-galaxy-s4
ከኢንተርኔት መስፋፋት ጋር ተያይዞ በ1990ዎቹ ካሜራ ያላቸው፣ ሙዚቃ የሚያስደምጡ፣ ጨዋታዎች ያላቸው፣ ፈጣን የሆኑ ስልኮች ቀስ በቀስ ወደ ህዝቡ እየደረሱ መጡ። አሜሪካዊው ድርጅት አፕል ያስተዋወቀው አይ ፎን (iPhone) በተንቀሳቃሽ ስልክ እድገት ላይ ትልቅ አሻራን የተወ ፈጠራ ነበር። ድርጅቱ በተከታያይ እያሻሻለ የሚያወጣቸው ስልኮች በጉጉት የሚጠበቁ ሲሆን ተፎካካሪ ምርቶችን የሚያመርቱት እነ ሳምሰንግ፣ ሶኒ፣ ሞቶሮላ እና ሌሎችም የተንቀሳቃሽ ስልክን ቴክኖሎጂ ወደፊት እያበረሩት ነው። የተንቀሳቃሽ ስልክ ቴክኖሎጂ ድምጽ ብቻ ከሚያስተላልፈው አንደኛ ዘመን (1G)፣ የጽሁፍ ማስተላለፍን በመጨመር ወደ ሁለተኛ ዘመን (2G)፣ ከዛም ኢንተርኔት መጠቀም እና ስዕልም ሆነ ፋይሎችን ማስተላለ የሚያስችለው ሶስተኛ ዘመን (3G) አልፎ አሁን ፈጣን ቪዲዮ እና ሌሎች ትልልቅ መጠን ያላቸው መረጃዎችን ማስተላለፍ የሚያስሽል አራተኛ ዘመን (4G) ላይ ደርሶአል።
ለወደፊት ተጣጣፊ የሆኑ የገንዘብ አጠቃቀምን ጨምሮ በርካታ የማህበራዊ ህይወታችን ውስጥ ትልቅ ድርሻ የሚኖረው ከኢንተርኔት ጋር በቀላሉ የሚያገኘን ሆኖ ይቀጥላል።

ወደፊት የሚጠበቁ ተጣጣፊ ተንቀሳቃሽ ስልኮች

ወደፊት የሚጠበቁ ተጣጣፊ ተንቀሳቃሽ ስልኮች

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s