ባየር ሙኒክ የዘንድሮ የጀርመን ቡንደስ ሊጋ አሸናፊ መሆኑን አረጋገጠ

bundesliga

ታዋቂው ባየር ሙኒክ ገና 6 ጨዋታ የሚቀረውን የቡንደስሊጋ ውድድር ለ23ኛ ግዜ አሸናፊነቱን ያረጋገጠው ባሳለፍነው ቅዳሜ ከሜዳቸው ውጪ ኢንትራክት ፍራንክፉርት 1-0 በሆነ ጠባብ ውጤት በማሸነፍ ነው። በሊጉ በሁለተኛነት የሚከተለው የአምናው ሻምፒዮና ዶርትመንድ ሲሆን 6 ጨዋታ እየቀረ በመካከላቸው የ20 ነጥብ ልዩነት በመኖሩ ባየርን አሸናፊ ነቱ ታውቋል።
ባለፈው አመት በተሳተፈበት ሶስት ትልልቅ ውድድሮች ማለትም የሃገር ውስጥ ሁለት ውድድሮች እና በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ በሙሉ ሁለተኛ ሆነው ማጠናቀቃቸው ያናደዳቸው ባየርኖች በዘንድሮ አመት ካደረጉት 28 የሊግ ጨዋታ አንድ ሽንፈት ብቻ በማስተናገድ ውድድሩን በአንደኝነት አጠናቀዋል። በዘንድሮ የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግም ወደ ግማሽ ፍጻሜ ለማለፍ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን 2-0 በማሸነፍ እድላቸውን ያሰፉ ሲሆን በጀርመን ካፕ ውድድርም ግማሽ ፍጻሜ ውስጥ በመግባታቸው ተጨማሪ ዋንጫ ያገኛሉ ተብሎ ይገመታል። በመጪው አመት ዝነኛው የቀድሞ የባርሴሎና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ክለቡን በአሰልጣኝነት እንደሚይዘው መገለጹ ይታወቃል። [ፎቶ: scmp]

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s