ማንቸስተር ዩናይትድ የ2012/2013 የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ሻምፒዮን መሆኑን አረጋገጠ

united

ማንቸስተር ዩናይትድ ሮበን ቫን ፐርሲ ባገባቸው 3 ጎሎች አስቶንቪላን 3-0 ባሸነፈበት ጨዋታ ክለቡ ለ20ኛ ግዜ የእንግሊዝ ሻምፒዮን ሆኗል። ባለፈው አመት በመጨረሻው ጨዋታ በመጨረሻ ደቂቃው ላይ በከተማው ተቀናቃኝ ማንቸስተር ሲቲ ዋንጫውን የተነጠቀው ዩናይትድ ዘንድሮ 4 ጨዋታ እየቀረ በሁለተኛነት ከሚከተለው ማንቸስተር ሲቲ የ16 ነጥብ ልዩነት በመያዙ አሸናፊ ሆኗል።

በጨዋታው ሃትሪክ የሰራው ቫን ፐርሲ ለቡድኑ 24 ጎሎችን አስቆጠሮ 8 ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን በማቀበል ቡድኑ ለዋንጫ ያደረገውን ግስጋሴ ላይ ትልቅ አሻራ ያሳረፈ ሲሆን እንግሊዛዊው ዋይን ሩኒ በተሳተፈበት 25 ጨዋታ 12 ጎሎችን በማግባት እና 10 ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን በማቀበል ቡድኑን አግዞአል። የዘንድሮ የሊጉ ኮኮብ ተጫዋች ምርጫ ላይ የተካተተው ማይክል ካሪክም በዘንድሮ አመት መሃል ሜዳ ጨዋታዎችን በመቆጣጠር በኳስ አጨዋወት መብሰሉን ያስመሰከረ ሲሆን መቼም የማይደክመው የ39 አመቱ ራያን ጊግስ 13ኛ የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫውን ዛሬ አሸንፏል።

ሮበን ቫን ፐርሲ የጨዋታውን ሁለተኛ ጎል ካስቆጠረ በኋላ

ሮበን ቫን ፐርሲ የጨዋታውን ሁለተኛ ጎል ካስቆጠረ በኋላ

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s