ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ከ26 አመት ቆይታ በኋላ ከማንቸስተር ዩናይትድ አስልጣኝነት ሊለቁ ነው

siralex

እ.ኤ.አ በ1986 ዓ.ም ከሮን አትኪንስ በኋላ ማንቸስተር ዩናይትድን ማሰልጠን የጀመሩት ሰር አሌክስ ፈርጉሰን 13 የፕሪሚየር ሊግ፣ 5 የኤፍ ኤ ካፕ፣ 2 የቻምፒዮንስ ሊግ፣ 1 የአውሮፓ አሸናፊዎች አሸናፊ እና 1 የአለም ክለቦች ቻምፒዮን ጨምሮ 38 ዋንጫዎችን ከክለቡ ጋር በማግኘት የእንግሊዝ ውጤታማ አሰልጣኝ ከሆኑበት ቡድን ለመልቀቅ መወሰናቸውን ክለቡ ይፋ አደረገ። ከ11 አመት በፊት ከአሰልጣኝነት ለመልቀቅ የደረሱበትን ውሳኔ በባለቤታቸው ምክር ቀይረው በውጤታማነት የቀጠሉት ሰር አሌክስ ከቡድኑ የመልቀቃቸው ዜና ብዙዎችን አስደንግጧል።

በመጪው እሁድ በኦልድ ትራፎርድ በሚደረገው የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ደጋፊውን የሚሰናበቱ ሲሆን በክለቡ ውስጥ በሃላፊነት እና በአማካሪነት ደረጃ እንደሚቀጥሉ ታውቋል። ሰር አሌክስ የመልቀቃቸው ውሳኔ እጅግ ከባድ እንደሆነ ነገር ግን ግዜው ትክክለኛ እንደሆነ ተናግረዋል። “ክለቡን ጠንካራ አድርጎ መልቀቅ ወሳኝ ሲሆን እኔም ያንን አሳክቼ የሄድኩ ይመስለኛል” ብለዋል። ሲያክሉም “የዘንድሮ የእንግሊዝ ቻምዮን የሆነው ቡድን በጥሩ ብቃት ላይ የሚገኝ ሲሆን የአንጋፋ እና ወጣት ተጫዋቾች ስብጥሩም ጥሩ ነው። የታዳጊዎች ፕሮጀክቱም አስተማማኝ በመሆኑ ክለቡ በመጪዎቹ ግዜያት ጠንካራ ተወዳዳሪ እንደሚሆን አልጠራጠርም” የሚል አስተያየት ሰጥተዋል። ባለቤታቸውን፣ የክለቡን ባለቤቶች፣ ደጋፊዎችን እና ተጫዋቾቻቸውንም አመስግነዋል ሰር አሌክስ።

ብዙዎች እሳቸውን ተክቶ የሚቀጥለው አስልጣኝ በውጤታማነት ለመቀጠል ብዙ ጫና እንደሚኖርበት እየተናገሩ ሲሆን የኤቨርተኑ ዴቪድ ሞየስ፣ የሮያል ማድሪዱ ጆሴ ሞሪንሆ ወይም የቦሪሲያ ዶርትመንዱ የርገን ክሎፕ ሊተኳቸው ይችላሉ እያሉ ነው።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s