ማህበረሰብ መሰረት ያደረጉ ባለ አነስተኛ የቴክኖሎጂ ፈጠራዎች በህንድ

ፕሮፌሰር አኒል ጉፕታ በተባሉ ባለሙያ መሪነት የተቋቋመ አንድ ተቋም በህንድ የተለያዩ ግዛቶች በመዘዋወር ማህበረሰቡን የሚጠቅሙ ባለአነስተኛ ወጪ የፈጠራ ስራዎችን ማገዝ እና ማበረታታት የጀመሩት ከ20 አመት በፊት ነበር። ባህላዊ እውቀቶችን፣ ዘመናዊ ሳይንስን እና በቅርብ የሚገኙ ግብዓቶችን በማጣመር የሚሰሩት እነዚህ ፈጠራዎች በአነስተኛ ገቢ ለሚተዳደረው አብዛኛው የህንድ ነዋሪ መፍትሄ እያበጁ ሲሆን እስካሁን ከ25000 በላይ ፈጠራዎች ወደ ምርት ተለውጠዋል። የተወሰኑት የፈጠራ ውጤቶች ከታች ቀርበዋል።

india1

ማንሱክ ፕራጃፓቲ እ.ኤ.አ በ2001 ዓ.ም በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ አካባቢውን ያለ ኤሌክትሪክ ሃይል ካስቀረ በኋላ ምግቦቻቸውን ለረጅም ግዜ ለማቆየት የሚረዳ ካለ ኤሌትሪክ የሚሰራ ማቀዝቀዣ በጭቃ በማዘጋጀት የፈጠራ ተሸላሚ የሆነ ሲሆን ህብረተሰቡ በአነስተኛ ወጪ ማቀዝቀዣውን በመግዛት ምግቦቻቸውን ለ5 ቀናት ያህል ሳይበላሹ ማቆየት ችለዋል። በፈጠራው በርካታ ሽልማቶች የተቀበለው ማንሱክ መብራት ላልተዳረሰባቸው የሃገሪቱ የገጠር ክፍሎችም ማቀዝቀዣውን በማቅረብ ገቢውን ማጠናከር ችሎአል።

india2

ማንሱክባይ ጃጋኒም ህንድ ውስጥ በብዛት የሚገኙ የተበላሹ ሞተር ብስክሌቶችን እንዴት በቀላሉ ወደ አነስተኛ ትራክተርነት እንደሚቀየሩ በማሳየት ብዙዎች የግብርና ምርታቸውን እንዲያሻሽሉ የሚያግዝ ፈጠራ ባለቤት ነው።

india3

ይህንን አነስተኛ ወጪ ፈጠራ ድርጅቶችም እያገዙት ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 8ሺ የአሜሪካ ዶላር የሚያወጣው በእጅ የሚያዝ ተንቀሳቃሽ አልትራ ሳውንድ መሳሪያ አንዱ ነው። ገንዘቡ ውድ ቢመስልም በሆስፒታሎች የሚገኘው አልትራ ሳውንድ መሳሪያ ወደ 150ሺ ዶላር የሚያወጣ በመሆኑ ፈጠራው ዋጋውን በ20 እጥፍ የቀነሰ እና የህክምና አገልግሎት በቅርብ የማያገኙ እርጉዝ እናቶች በቤታቸው ምርመራዎችን እንዲያካሂዱ ያስቻለ ነው።

ከነዚህ ውጪ የውሃ መሳቢያዎች፣ አነስተኛ የሃይል ማመንጫዎች እና በርካታ ማሽኖችም በዚሁ ፕሮግራም ተሰርተው ህዝቡን እያገለገሉ ይገኛሉ። [CNN]

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s