ኔልሰን ማንዴላ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

POTD-mandela_2617707b

ለደቡብ አፍሪካ ጥቁሮች መብት የታገሉት እና ረጅም አመታትን በአፓርታይድ አገዛዝ የታሰሩት ኔልሰን ማንዴላ በ95 አመታቸው አረፉ። መታሰር ከሚያደርጉት ትግል ያላገዳቸው ማንዴላ ያካሄዱት ሰላማዊ ትግል ፍሬ አፍርቶ ከእስር ሲፈቱ የደቡብ አፍሪካ የመጀመሪያው ዲሞክራሲያዊ መሪ መሆን ችለው ነበር። የሃፈሬው ህዝብ ማዲባ ብሎ የሚጠራቸው የነጻነት ፈርጥ አመራራቸውን የጀመሩበት ይቅር መባባልን እና እርቅን ያስቀደመው ዝግጅት የአፓርታይድን ስርዓት ጠባሳ ለማጥፋት ያበረከተው ሰላማዊ አስተዋጽኦ የኖቤል የሰላም ተሸላሚ ያደረጋቸው ማንዴላ አፍሪካ ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ከአንድ አመራር ግዜ በኋላ ስልጣናቸውን በሰላም የለቀቁ መሪ ሆነው ታሪክ ሰርተዋል። በቅርቡ በበረታባቸው የሳንባ በሽታ ምክንያት በተደጋጋሚ ህክምና ሲያገኙ የቆዩት ማዲባ በቤታቸው ውስጥ የሃኪም ክትትል እየተደረላቸው ነበር።

ለትግላቸው የሚሆን ድጋፍ ለማሰባሰብ የተለያዩ አገራትን ሲጎበኙ ኢትዮጲያ በመምጣት የወታደራዊ እና ፖለቲካዊ አመራር ስልጠና የወስዱት ማንዴላ በኢትዮጲያ አየር መንገድ ሲበሩ ከተመለከቱት ጥቁር አብራሪ ጀምሮ በነበራቸው ቆይታ ሁሉ ኢትዮጲያ የማይረሳ ግዜ ስለማሳለፋቸውን እንዲህ ብለው ነበር።

ኢትዮጲያ በውስጤ ውስጥ የተለየ ቦታ ያላት አገር ናት። ኢትዮጲያን መጎብኘት እንግሊዝ፣ ፈረንሳይ እና አሜሪካንን በአንድ ላይ ከመጎብኘት የበለጠ ይማርከኛል። ኢትዮጲያ መሄድ የአፍሪካዊነት መሰረቴን እና ማንነቴን እንደ ማግኘት ነው የሚሰማኝ።

ለማንዴላ የተሰጣቸው የኢትዮጲያ ፓስፖርት

ለማንዴላ የተሰጣቸው የኢትዮጲያ ፓስፖርት

የማዲባ ሞት ከተሰማበት ደቂቃ ጀምሮ የተለያዩ ታዋቂ ሰዎች፣ መሪዎችን ጨምሮ በርካቶች ለማንዴላ ያላቸውን አድናቆት፣ ክብር እና በማለፋቸው የተሰማቸውን ሃዘን በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች እያስተጋቡ ይገኝሉ።  

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s