አንዲት ቀጫጫ ሴት ሁለት ኪሎ የተጠበሰ ስጋ ከሶስት ደቂቃ ባነሰ ግዜ በመብላት አዲስ የአለም ሪከርድ አስመዘገበች

በአሜሪካን አገር ታዋቂ የሆነ የሬስቶራንቶች አሰራር አለ። ይሀውም እጅግ ትልቅ ምግብ አዘው ብዙ ግዜ ሳይወስዱ በልተው ለሚጨርሱ ሰዎች የበሉበት ክፍያ አይጠየቁም። መብላት የሚጠበቅባቸው ምግብ እጅግ ብዙ ቢሆንም በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ይህንን ውድድር በመሞከር ገንዘባቸውን ይከስራሉ። በቅርቡ በፖርትላንድ ግዛት የሚገኝ ሬስቶራንት ውስጥ ጎራ ያለች ተወዳዳሪ ተመጋቢ 2 ኪሎ ስጋ መብላት እንደምትችል ተናግራ ውድድሩን ስትጀምር ማንም ይሳካላታል ብሎ አልጠበቀም ነበር።

ሞሊ ሹላየር የተባለችው የአራት ልጆች እናት ግን በ2 ዲቂቃ ከ45 ሰከንድ ሁለት ኪሎውን ስልቅጥ በማድረግ አዲስ የአለም ሪከርድ አስመዝግባለች። በሃይለኛ ተመጋቢነቷ የምትታወቀው ሞሊ ከአንድ ቀን በፊት ወደ ሌላ ሬስቶራንት ጎራ ብላ 5 ኪሎ ሳንድዊች በግማሽ ኪሎ ድንች ጥብስ በመብላት ሪከርድ ሰብራ ከሬስቶራንቱ የ650 ዶላር ሽልማት አግኝታ ነበር። ስምንተኛው ሺ!! [Dailymail]

ስትበላ የተቀረጸውን ቪዲዮ ከስር ይመልከቱ።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s