ፌስቡክ ከፍት የእውቀት ሽግግርን በማገዝ ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ ከብክነት አዳነ

ፌስቡክ

በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ስርዓት ውስጥ የሚዘወተር ክፍት የእውቀት ሽግግር የሚባል አስተሳሰብ አለ። ከኮምፒውተር ውጪ መድሃኒት እና የመሳሰሉ ዘርፎች ውስጥም የሚንጸባረቀው ይህ አስተሳሰብ “የሰውን ልጅ እውቀት እና ምርቶች አሰራር ለሌሎች ካለምንም ክፍያ በማሳየት በተከታታይ በሚደረጉ የጋራ ውይይቶች እና ስራዎች የምርቱን ጥራት መጨመር ይቻላል” ብሎ ያምናል። በህብረት ተሰርተው እና ዳብረው የሚወጡት የኮምፒውተር ፕሮግራሞች ለተጠቃሚ ነጻ ቢሆኑም በክፍያ ከሚገዙት ፕሮግራሞች የማይተናነሱ እና አንዳንዴም የተሻሉ ሆነው ተገኝተዋል።

ማንኛውም የኢንተርኔት ተጠቃሚ ምንም አይነት ክፍያ ሳያገኝ በነጻ መረጃዎችን የሚያስገባበት እና በኢንተርኔት ላይ በነጻ የመረጃ ምንጩነቱ የሚታወቀው ዊኪፔድያ በሽያጭ ይቀርብ የነበረውን የማይክሮሶፍት ኢንሳይክሎፒዲያ ከገበያ ውጪ አድርጎታል። በርካታ የመረጃ አስገቢዎች ያሉት ዊኪፔድያ በሚይዘው መረጃ ብዛትም ከማይክሮሶፍት ምርት እጅግ የላቀ መሆኑ ደግሞ የዚህን አስተሳሰብ ጠቃሚነት የሚያጎላ ነው። የኮምፒውተር አሰራርን የሚቆጣጠረው ዋንኛ ፕሮግራም ማይክሮሶፍት ዊንዶውስ እስከ 200 ዶላር የሚያስወጣ ሲሆን ተጨማሪ ሶፍትዌሮችንም ለመጠቀም ክፍያ ይጠይቃል። ከዚህ ጋር የሚፎካከሩ ሊነክስ የተሰኙ ምርቶች በነጻ የሚገኙ ሲሆን ተጨማሪ ሶፍትዌሮችም እንዲሁ በነጻ የሚቀርቡ ከመሆናቸው ሌላ በቫይረስ የማይጠቁ መሆናቸው ተፈላጊ ያደርጋቸዋል። በአሁኑ ሰአት በአለማችን ካሉ 500 ትላልቅ ኮምፒውተሮች ውስጥ 95% የዚህ የነጻ ፕሮግራም ተጠቃሚዎች ናቸው።

ይህንን ጽንሰሃሳብ መሰረት በማድረግ ፌስቡክ ከአንድ ቢሊዮን በላይ የደረሱትን ተጠቃሚዎቹን መረጃ የሚያስቀምጥበት ትላልቅ የኮምፒውተር መረጃ ማስቀመጫዎች እና የሚቀመጡበትን ቦታ ዲዛይን ስራ ላይ እውቀት ያላቸው ሰዎች ተሳትፎ እንዲያደርጉ እና ስራው ለማንኛውም ድርጅት መጠቀሚያ እንዲሆን በማድረጉ ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ አድኗል። እነዚህ ትላልቅ የመረጃ ማስቀመጫዎች በኤሌትሪክ የሚሰሩ እና ትልቅ ሃይል የሚያባክኑ በተጨማሪም የሚፈጥሩትን ሙቀት ለመቆጣር የሚያርፉበት ቦታ ስራ ከፍተኛ ወጪ የሚያስወጣ ሲሆን በነጻ የተሰባሰቡት ባለሙያዎች ያመጡት ሃሳብ እጅግ ሃይል ቆጣቢ የሆኑ ምርቶች የሚሰሩበትን መንገድ በመቀየስ ፌስቡክ ለግንባታ፣ ለአካባቢ ጥበቃ እና ለኤሊክትሪክ ሃይል ያወጣ የነበረውን ብዙ ገንዘብ ማትረፍ ችለዋል። [Techcrunch]

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s