በአለማችን ላይ ምን ያህል ገንዘብ አለ?

የሰው ልጅ በገንዘብ መገበያየት ከመጀመሩ በፊት የንግድ ሂደት የሚከናወነው እቃዎችን በመቀያየር ነበር። የገንዘብ ንድፈ ሃሳብ ተነድፎ ለመገበያያነት መጠቀም ከተጀመረ ከሶስት ሺ አምስት መቶ አመታት በላይ ቢያስቆጥርም ብዙዎች አሁንም ገንዘብን ከመጠቀም ውጪ ስለ አጠቃላይ የገንዘብ ስርዓቱ ያላቸው እውቀት አነስተኛ ነው። ብዙዎች ከሚያነሱት ገንዘብ ጋር የተይያዘ ጥያቄ አንዱ “በአለም ላይ ምን ያህል ገንዘብ አለ?” ነው።

በአለም ላይ የሚንቀሳቀሱ የገንዘብ አይነቶች በአራት ይከፈላሉ። ኤም 0 የሚባለው የመጀመሪያው አይነት ገንዘብ በወረቀት ኖት ወይም በሳንቲም መልክ ታትሞ በህዝቡ ውስጥ የሚዘዋወር ገንዘብ ሲሆን በአለም ባሉ ሃገራት በሙሉ ያለው ኤም 0 ገንዘብ ዋጋው ወደ 5 ትሪሊዮን ዶላር አካባቢ ነው። ቀጣዪ ኤም 1 የሚባለው ኤም 0 ውስጥ ያሉትን የወረቀት እና የሳንቲም ገንዘብ በተጨማሪ በተንቀሳቃሽ ሂሳብ ባንኮች ውስጥ የተቀመጠ ገንዘብንም የሚያካትት ሲሆን በአለም ላይ ያለው የኤም 1 መጠን ወደ 25 ትሪሊዮን ዶላር ይጠጋል። ሶስተኛው ኤም 2 የሚባል ሲሆን ኤም 1 ከሚያካትታቸው የገንዘብ አይነቶች በተጨማሪ በቁጠባ ሂሳብ ባንክ ውስጥ የተቀመጠ ገንዘብ አካቶ ይይዛል። በዚህ ቡድን ያለው የገንዘብ መጠን ወደ 60 ትሪሊዮን ዶላር ይጠጋል። የመጨረሻው የገንዘብ አይነት ኤም 3 ከላይ የተዘረዘሩትን የገንዘብ አይነቶች በተጨማሪ በጣም ረጅግ መክፈያ ግዜ ያላቸው ብድሮች፣ የአለም አቀፍ የገንዘብ ሽያጭ ገበያዎች ውስጥ ያለ ገንዘብ እና በኦፊሴላዊ ሪፖርት የማይገለጹ ገንዘቦችን የሚያካትት ሲሆን አጠቃላይ መጠኑ ወደ 75 ትሪሊዮን ዶላር ይገመታል። እናም በአለም ላይ ያለው ገንዘብ ለሁላችንም እኩል እኩል እንካፈል ቢባል ህጻናትን ጨምሮ እያንዳንዱ ሰው ከ10ሺ የአሜሪካ ዶላር በላይ ይደርሰናል ማለት ነው።

ስለገንዘብ ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ ቪዲዮውን ይመልከቱ!

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s