ጀርመን ከማንኛውም አገር የሚመጡ ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርትን በነጻ እንዲማሩ ፈቀደች

ዩንቨርስቲ ትምህርት

ዩንቨርስቲ ትምህርት

በጀርመን ሃገር የሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ዩንቨርስቲዎች በሙሉ በአሁኑ ሰዓት ለመማር የሚፈልግ ማንኛውም ተማሪ የትምህርት ክፍያ አይጠይቁም። ክፍያ ያስጠይቅ የነበረ አንድ ዩንቨርስቲ ሰሞኑን የክፍያ ስርዓቱን በመሰረዙ በሃገሪቷ ለመማር አመልክቶ ተቀባይነት ያገኘ ተማሪ ትምህርቱን በነጻ ይከታተላል ማለት ነው።

ወደዚህ ውሳኔ እንዴት እንደመጡ አንድ የህዝብ ተወካይ ሲያስረዱ የክፍያ መኖር የተማረ ወላጆች የሌላቸውን ወጣቶች ከመማር የሚያሰናክል ስለሆነ ነው ብለዋል። የፖለቲካ ስርዓቱ ወጣት ሴቶች እና ወንዶች ካለምንም ችግር ጥራት ያለው ከፍተኛ ትምህርት እንዲያገኙ ማስቻሉን ተናግረዋል።

የክፍያ ስርዓቱ በስራ ላይ እያለ እንኳን የጀርመን ዩንቨርስቲዎች በአማካይ በአመት 1260 የአሜሪካን ዶላር የሚያስከፍሉ ሲሆን በአሜሪካን አገር የሚገኝ ተማሪ በበኩሉ በአመት የ29000 የአሜርካን ዶላር ባለዕዳ ይሆን ነበር። በተጨማሪም ጀርመን ለተማሪዎች ቅናሽ ያለው ምግብ፣ ልብስ እና መዝናኛ ዝግጅት የምታቀርብ ሲሆን የህዝብ መጓጓዣም ለተማሪዎች ነጻ ነው።

ኪው ኤስ የተባለ ተቋም በሚያወጣው የዩንቨርስቲዎች ደረጃ መሰረት ቀዳሚዎቹ ሶስት ዩንቨርስቲዎች ሃይድልበርግ ዩንቨርስቲሙኒክ ቴክኒካል ዩንቨርስቲ እና ላውዲግ ማክሲሚላን ሙኒክ ዩንቨርስቲ ናቸው። [Dailycos]

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s