የእሁድ ጥያቄ ጨዋታ 2 – ካለፈው ሳምንት ጥያቄ መልሶች ጋር

ጨዋታዎች

ባለፈው ሳምንት በተጀመረው የእሁድ ጥያቄዎች መሰረት የዚህ ሳምንት ሁለት ጥያቄዎች ቀርበዋል መልሶን አስተያይት መስጫው ላይ ይተዉ።

ያለፈው ሳምንት ጥያቄ መልሶችም ከታች ቀርበዋል።

1. ሁለት ጓደኛሞች ሰለሞን እና አዲሱ አሉ። አዲሱ ከሰለሞን ኋላ ቆሞ ሰለሞንም ከአዲሱ ኋላ ቆሟል። ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል?

ጓደኛሞች

2. ከስር ያለው ሰዕል ላይ ያለው የሳንቲሞች ሶስት ጎን የፒራሚድ ቅርጽ አለው። ሶስት ሳንቲሞችን ብቻ በማንቀሳቀስ ሶስት ጎኑ የተገለበጠ ፒራሚድ ቅርጽ እንዲይዝ ለማድረግ የትኞቹን ሳንቲሞች ያንቀሳቅሳሉ?

አስር ሳንቲም

~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~

ያለፈው ሳምንት ጥያቄ መልሶች እንደሚከተለው ቀርበዋል።

1. የመጀመሪያውን ጥያቄ መልስ ለመረዳት ትንሽ ቁጥር ደማሪ ወይም ቁማርተኛ መሆን ይጠይቃል። ከሶስት በሮች ውስጥ ሽልማት ያለው በአንዱ በር ብቻ ከሆነ በእያንዳንዱ በር ጀርባ ሽልማት የመገኘት እድሉ አንድ ሶስተኛ (1/3)ነው። እርሶም ከነዚህ አንዱን ቢመርጡ የእድለኛነቶ መጠን አንድ ሶስተኛ (1/3) ሲሆን የመሳሳት እድሎ ደግሞ ሁለት ሶስተኛ (2/3) ነው። አሁን ሰውየው ከሁለቱ አንዱን ከፍቶ ሽልማቱ እዛ ውስጥ እንደሌለ ካሳዮት እና ወደ ቀረው በር መቀየር እንደሚፈልጉ ቢጠይቆት ሳያቅማሙ እሺ ብለው መመለስ አለቦት። ሰውየው ከከፈተው በር ጀርባ ምንም ሽልማት ከሌለ መጀመሪያ የመረጡት በር ትክክለኛነት አሁንም አንድ ሶስተኛ ሲሆን መጨረሻ የቀረው በር ትክክለኛነት ደሞ ሁለት ሶስተኛ ሆነ ማለት ነው። ስለዚህ እድሎን ለማስፋት ወደቀረው በር ቢለውጡ ይመከራል።

2. ሁለተኛው ጥያቄ አምስት ቅርጾችን ገጣጥሞ አራት ማዕዘን መስራት ነው መልሱ ከታች ይመልከቱ

አራት ጎን

3 Comments

Leave a reply to Anonymous Cancel reply