አንዲት የ16 አመት ወጣትን ህይወት የቀጠፈ እጅግ አስከፊ ወንጀል

ፍትህ ለሴቶች

የ10ኛ ክፍል የማሪ የሆነችው ሃና ላላንጎ ትምህርት ቤት ውላ ወደ ቤቷ ለመሄድ በተሳፈረችበት ታክሲ ውስጥ በየነበሩ ወንጀለኞች ከተጠለፈች በኋላ ለረጅም ቀናት በደረሰባት አስጸያፊ ጾታዊ ጥቃት ምክንያት ህይወቷ አለፈ። ከአየር ጤና ወደ ጦርሃይሎች የሚሄድ ታክሲ ውስጥ በጩቤ በማስፈራራት የታፈነቸው ሃና ከ 10 ቀናት በላይ በእገታ ላይ ከቆየች በኋላ መንገድ ላይ የጣሏት ሲሆን ሆስፒታል ደርሳ አስቸኳይ ህክምና ቢደረግላትም ከጉዳቷ አስከፊነት የተነሳ ህይወቷ አልፏል።

ጠላፊዎቹ ከቤተሰቦቿ ጋር ግንኙነት የጀመሩ ሲሆን እህቶቿን ከእሷ ጋር እናገናኛችሁ በማለት ወደ ተመሳሳይ ታክሲ ለማስገባት ሙከራ ሲያደርጉ ታርጋቸው በመመዝገቡ ሊያዙ ችለዋል። ፖሊስ ተጠርጣሪዎችን ወደ ሆስፒታል በመውሰድ በተጎጂዋ እንዳስለየ ተሰምቷል።

ከፍርድቤት ከባድ ቅጣት እንጠብቃለን።[ሪፖርተር]

Advertisements

ጥሩነሽ ዲባባ የመጀመሪያ የማራቶን ውድድሯን በሶስተኛነት አጠናቀቀች

ጥሩነሽ ዲባባ

ጥሩነሽ ዲባባ

ዛሬ በተካሄደው ታዋቂው የለንደን ማራቶን ላይ የተሳተፈችው አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ 2 ሰአት ከ20 ደቂቃ ከ35 ሰከንድ በመግባት የመጀምሪያ የማራቶን ውድድሯን በሶስተኛነት አጠናቃለች። ከባድ ከሚባሉ የማራቶን ውድድሮች አንዱ በሆነው በዚህ ማራቶን ውድድር ኢድና ኪፕላጋት እና ፍሎረንስ ኪፕላጋት የተባሉ ኬንያውያን ከጥሩነሽ በ14 እና በ11 ሰከንድ ቀድመው በመግባት አንደኛ እና ሁለተኛ ሆነው አጠናቀዋል። እስካሁን በአብዛኛው በ5ሺ እና 10ሺ ውድድሮች ላይ ብቻ ተወዳዳሪ የነበረችው ጥሩነሽ ከውድድሩ በኋላ እንደ መጀመሪያ ማራቶንነቱ በውጤቷ ደስተኛ መሆኗን እና ወደፊት በሚካሄዱ የማራቶን ውድድሮች ላይ እንደምትሳተፍ ለጋዜጠኞች ተናግራለች። ጥሩነሽን በመከተል ፈይሴ ታደሰ እና አበሩ ከበደ 4ኛ እና 5ኛ ሆነው ሲጨርሱ የለንደን ኦሎምፒክ የማራቶን የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ቲኪ ገላና ውድድሩን በ9ኛነት አጠናቃለች።

በወንዶቹ ውድድርም የመጀመሪያ ማራቶኑን የሮጠው በትውልድ ሶማሊያዊ በዜግነት እንግሊዛዊው ሞ ፋራህ ውድድሩን በ8ኛነት ሲያጠናቅቅ በዚህ ውድድር ጸጋዬ ከበደ፣ አየለ አብሽሮ እና ጸጋዬ መኮንን ከ3ኛ እስከ 5ኛ ያለውን ደረጃ በመያዝ ውድድሩን ጨርሰዋል። ሌላው ኢትዮጲያዊ አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ 9ኛ እና ኤርትራዊው ሳሙኤል ፀጋዬ 16ኛ ደረጃን በመያዝ ማራቶኑን አጠናቀዋል።

ሸንቀጥ ያሉ ሴቶች የተሻለ ጤናማ እና የዳበረ አእምሮ እንዳላቸው በጥናት ማረጋገጡን ታዋቂው የዩንቨርሲቲ ኦፍ ኦክስፎርድ አስታወቀ።

ethiopianzxy1

በ16ሺ ሴቶች ላይ ጥናት ያደረጉት በርካታ ሳይንቲ ስቶች እንዳስረዱት ከአማካይ መጠን ተለቅ ያለ ቂጥ ያላቸው ሴቶች ከሌሎች ሲወዳደሩ የተሻለ እውቀት ባለቤት ብቻ ሳይሆኑ በሽታን የመቋቋም አቅማቸውም በዛ ያለ ነው። ጥናቱ እንዳስረዳው ጥሩ አቋም ያላቸው ሴቶች አነስተኛ የኮሌስትሮል መጠን እና ስኳርን የሚበታትን ኢንዛይም ስለሚያመነጩ በልብ ድካም እና ስኳር የመጠቃት እድላቸው አነስተኛ ነው።

ይህ ጥሩ ጎን የሚታየው በሴቶች ላይ ብቻ ሳይሆን በልጆቻቸውም ላይ እንደሆነ ተነግሯል። እናም ጥሩ ቅርጽ ካላት እናት የተወለዱ ልጆች አነስተኛ ከሆነች ሴት ልጆች የተሻሉ ጎበዞች መሆናቸውን መረጃቸው አሳይቷቸዋል።

ፕሮፌሰር ቆንስጣንጢኖስ ማኖፑሎስ በተባሉት ምሁር መሪነት የተጀመረው የኦክስፎርድ ውጤት በሌሎች ታዋቂ በሆኑ በካሊፎርኒያ እና ፒትስበርግ ዩንቨርስቲዎች በተደረጉ ጥናቶችም ታይተው ነበር። [elitedaily]

በእርሶ አስተያየት በ2005 ዓ.ም ኢትዮጲያ ውስጥ ትልቅ ተሰሚነት የነበራቸው ሴቶች እነማን ናቸው?

ethiopian women

ባለፉት አመታት ኢትዮጲያ ውስጥ ተሰሚነት ያላቸውን ሴቶች ዝርዝር ስናቀርብ ነበር። የዚህን አመት ዝርዝር ከማዘጋጀታችን በፊት አንባቢዎችም ተሳትፎ እንዲያደርጉ ታስቧል። እናም በተሰማሩበት የስራ ዘርፍ ያላቸውን ውጤታማነት ፣ በመገናኛ ብዙሃን የሚነሱበት መጠን እና በአጠቃላይ በአብዛኛው ህዝብ ያላቸውን ተደማጭነት  መሰረት በማድረግ በጣም ተቀባይነት አላቸው የሚሏቸውን ብዛታቸው ከ10 ያልበለጡ ሴቶችን በእጩነት እንዲያቀርቡ ተጋብዘዋል። በእጩነት የሚያቀርቡት ሰው ብዛት ከ10 ቢያንስ ችግር የሌለው ሲሆን እስከ መስከረም 9, 2006 ዓ.ም (September 20, 2013) ድረስ ጥቆማዎን በሚከተሉት ኢሜል አድራሻዎች ወይም ከስር ባለው አስተያየት መስጫ  እንቀበላለን።

Email – meti@thearadaonline.com

editor@thearadaonline.com

ወደ ህዋ የመጠቀች ተመራማሪ መንኩራኩር ውስጥ ጸጉሯን ስታጥብ

በተደጋጋሚ ከሚደረጉት የአለም አቀፍ ህዋ ምርምር ጉዞዎች አካል በሆነ የህዋ ቡድን 36 ተጓዥ የሆነችው አሜሪካዊቷ ካረን ናይበርግ የመሬት ስበት በሌለበት መንኩራኩር ውስጥ ጸጉሯን ስታጥብ።

ወንዶች የወሊድን ህመም ይቋቋሙታል?

hsss

በብዙ ባሎች ወይም ወንዶች የመታመነው ሴቶች የወሊድ ህመምን እንደሚያካብዱት እና ያን ያህል ከባድ እንዳልሆነ ቢሆንም እናቶች ግን ለሰአታት ሊቆይ የሚችለውን ምጥ እና ወሊዱን ህመም የሚቋቋም ወንድ ልጅ እንደማይኖር በድፍረት ይናገራሉ።

ታዲያ ይህንን ለዘመናት የቆየ ክርክር ለመቋጨት ሁለት የሆላንድ ጋዜጠኞች የምጥ እና ወሊድ ህመሞችን ወንዶች ላይ መሞከር የሚያስችል ቴክኖሎጂ በመጠቀም ክርክሩን ፈተውታል። ጋዜጠኞቹ እራሳቸውን ከማሽኑ ጋር በማያያዝ ለሶስት ሰአት የምጥ እና የሰላሳ ደቂቃ ወሊድ ህመሞችን ለመስማት ተዘጋጅተው ቢገቡም የምጥ ህመሙን ለሁለት ሰአት ብቻ በመቋቋም አቋርጠውታል። ተጨማሪ የአንድ ሰአት ተኩል ህመም የሚቋቋሙበት ሁኔታ እንደሌለ በመናገር ሴቶች እየተናገሩ የነበረው ትክክል እንደሆነና ከባድ እንደሆነ አስረግጠዋል።

ሴቶች እንኳን ደስ አላችሁ!!

 የጋዜጠኞቹን ዝግጅት ቀጣዩ ቪዲዮ ላይ ይመልከቱ። [Gawker]

ሴቶች ላይ የሚደርስ ጥቃት ያበሳጨው ጋዜጠኛ

ስለ ሰው ልጅ መብት በሰፊው በሚወራበት እና መብቶች እንዲከበሩ ብዙ እርቀት በሚኬድበት አለማችን በሴቶች ላይ የሚደርስ ጥቃት አሁንም በብዙ ቦታዎች እየተሰማ ነው። በሃገራችን ኢትዮጲያም በሰፊው የሚታይ ችግር ሲሆን በቅርቡ እንኳን በብዙ መገናኛ ብዙሃን እንደተዘገበው ፍሬህይወት የተባለች እናት መሃል ከተማ ውስጥ በቀድሞ ባለቤቷ እና በሁለት ልጆቿ አባት በ18 ጥይት ተመታ መሞቷ ይታወቃል

በአሜሪካን አገር የሚኖር አንድ ጋዜጠኛም በቅርብ የሚያቃት ሴት በባለቤቷ መገደሏን አስከትሎ የችግሩን አስከፊነት ለማሳየት በሚል በወንዶች ጥቃት ሴቶችም ሆነ ህጻናት በሚሞቱ ግዜ ጸጉሩን በመላጨት የችግሩን ብዛት ለማሳየት አስቧል። እናም በተገደለችው ጓደኛው ምክንያት በቀጥታ በሚተላለፈው የቴሊቭዥን ስርጭት ጸጉሩን በመካጨት የጀመረ ሲሆን ፕሮግራሙን የተከታተሉ እና ስለ ውሳኔው የሰሙ ሰዎችም አብረውት ጸጉራቸውን ለመላጨት ማሰባቸው ታውቋል።

ኢትዮጲያ ውስጥ ትልቅ ተሰሚነት ያላቸው 10 ሴቶች ፡ እርሶም ሰው ይጠቁሙ

ከአንድ አመት ገደማ በፊት ኢትዮጲያ ውስጥ ተሰሚነት ያላቸው የመጀመሪያዎቹን 5 ታዋቂ ሴቶች ዝርዝር አቅርበን ነበር። (የባለፈውን አመት ዝርዝር ማየት ከፈለጉ እዚህ ይጫኑ )። አሁንም አመቱን ጠብቀን ከአንድ ወር በኋላ ቁጥራቸውን ወደ 10 ከፍ በማድረግ ተደማጭነት ያላቸው፣ ለብዙዎች አርአያ የሚሆኑ ሴቶቻችንን እናስታውሳለን።

ይህ በሚሳተፉበት ዘርፍ ያላቸውን ውጤታማነት ፣ በመገናኛ ብዙሃን የሚነሱበት መጠን እና በአጠቃላይ በአብዛኛው ህዝብ ያላቸውን ተደማጭነት  መሰረት በማድረግ የሚዘጋጅ ዝርዝር ዘንድሮ ደሞ አንባቢዎቻችንንም ለማካተት ታስቦአል። እናም እርስዎ በጣም ተቀባይነት አላቸው የሚሏቸውን ብዛታቸው ከ10 ያልበለጡ ሴቶችን በእጩነት እንዲያቀርቡ ተጋብዘዋል። በእጩነት የሚያቀርቡት ሰው ብዛት ከ10 ቢያንስ ችግር የሌለው ሲሆን እስከ ነሃሴ 30 2004 ዓ.ም (September 05, 2012) ድረስ ጥቆማዎን በሚከተሉት ኢሜል አድራሻዎች ወይም ከስር ባለው ፎርም እንቀበላለን።

 

መልካም የእናቶች ቀን

በዛሬው እለት የሚከበረው የእናቶች ቀን እናቶች በህብረተሰቡ ላይ ያላቸውን ተጽዕኖ የምናስብበት ቀን ነው። በሃገራችን ኢትዮጲያ ብዙ ያልተለመደው ይህ በአል በተወሰኑ ሰዎች ብቻ እናታቸውን በማሰብ እና ስጦታ በማዘጋጀት ተከብሮ ወይም ታስቦ ይውላል።

በየትኛውም ሃይማኖት፣ ጎሳ ወይም የፖለቲካ አስተሳሰብ ያለ ሰው ሁሉ ለእናቱ የተለየ አክብሮት እና ፍቅር አለው። ብዙ ጊዜአቸውን ጉልበታቸውን ለልጆቻቸው የሚሰጡት በርካታ እናቶች ለማንኛውም ውጤታማ ሰው መሰረት እንደሆኑ ጥርጥር የለውም። እናም አንድ ቀን ብቻ እናቶቻችንን በማስታወስ እና ያለንን አክብሮትእና ፍቅር ለእናቶቻችን ማሳየት ሳያንስ የሚቀር አይመስለኝም። ከዛ በተጨማሪ ደግሞ ይህንን ቀን በአገር ደረጃ በሰፊው በማክበር እናቶች ላይ ያሉ አሳሳቢ ችግሮችን ምፍትሄ የሚፈለግበት ሊሆን ይገባል። በተለይ በሃገራችን በተደጋጋሚ የሚያጋጥሙ ዘግናኝ የእናቶች ጥቃት ላይ አስፈላጊውን እርምጃ መውሰድ ይገባል። [ፎቶ David Burnett]

ለእናት ከተዜሙ ሙዚቃዎች መሃል የኔ ግብዣ፡ አስቴር አወቀ – እማምዬ