የማስመሰል ባለሙያዎች ፊልም ላይ የሚታይ ጉዳትን እንዲህ ነው የሚሰሩት

አንድን ፊልም በተመልካች ተወዳጅ ከሚያደርጉት ነገሮች አንዱ በሰው ዘንድ የሚታወቁ ነገሮች በፊልሙ ምን ያህል በትክክል መገለጻቸው ነው። ለምሳሌ በፊልም ላይ ያለ የካንሰር በሽተኛ ገጸባህሪ የጨረር ህክምና እየተከታተለ ቢሆን እውነተኛ አለም ላይ የሚያጋጥመውን የጸጉር መሳሳት እና መመለጥ በፊልሙም ላይ ማሳየት አስፈላጊ ነው። እንደዚህ አይነት ስራዎችን የሚሰሩ የማመሳሰል ባለሙያዎች ብዙ መንገዶች ተጠቅመው ፊልሙን ከእውነታ ጋር ያቀራርባሉ። ከታች ያለው ፊልም ላይ በአደጋ ምክንያት የሚከሰት ቁስልን ባለሙያዎቹ እንዴት እንደሚያስመስሉ ይመልከቱ።

Advertisements

ቴዲ አፍሮ – በሰባ ፸ ደረጃ

መጪውን አዲስ አመት ምክንያት በማድረግ ቴዲ አፍሮ አዲስ አበባ ውስጥ ራስ መኮንን ድልድይ አካባቢ በሚገኘው ሰባ ደረጃ ስም የተሰየመ እና ፒያሳን ፣ዝነኛዋን ሜሪ አርምዴን ፣ የኮሪያ ዘማቾችን ያስታወሰበትን ዘፈኑን ለቋል።

ሰባ ደረጃ

ሰባ ደረጃ

ሜሪ አርምዴ

ሜሪ አርምዴ

የፊልም ምርጫ – ዘ ዎልፍ ኦፍ ዎል ስትሪት (The Wolf of Wall Street)

ይህ የአለማችን ትልቁ የአስዮን ድርሻ ገበያ የሆነው እና በአሜሪካን አገር ኒውዮርክ ከተማ ውስጥ ዎል ስትሪት በሚባል ጎዳና ላይ መሰረቱን ያደረገው የኒውዮርክ አክስዮን ድርሻ መገበያያ ማዕከል ውስጥ የሚሰራ ደላላ ህይወት ላይ ያጠነጠነ ፊልም ነው። በእውነተኛ ታሪክ ላይ ተመስርቶ የተሰራውን ይህንን ፊልም ዝነኞቹ ሊዮናርዶ ዲካፕሪዮ እና ማቲው ማኮግንሄይ ይተውኑበታል። የአለምን ኢኮኖሚ የሚነዳው የዚህ ማዕከል አሰራር ትንሽ ማወቅ ከፈለጉ በሚያዝናና መልኩ የሚያሳይ ፊልም ነው። የፊልሙ ማስታወቂያ ይመልከቱት።

የሙዚቃውን አለም እያነጋገረ ያለ ትውልደ ኢትዮጲያዊ ሙዚቃኛ

አቤል ተስፋዬ (The Weekend)

አቤል ተስፋዬ (The Weekend)

“ዘ ዊኬንድ” በሚል የመድረክ መጠሪያ የሚታወቀው እና በካናዳ ሃገር የሚኖር ትውልደ ኢትዮጲያዊ አቤል ተስፋዬ ከሶስት አመታት በፊት በኢንተርኔት መልቀቅ በጀመረው የሙዚቃ ስራዎቹ ከፍተኛ እውቅናን አግኝቶ በቅርቡ የሚተሙ የሚዲያ ውጤቶች እና በርከት ያሉ የሙዚቃ አድናቂዎች ከፖፕ ሙዚቃ ንጉሱ ማይክል ጃክሰን ጋር እያወዳደሩት ይገኛሉ። እ.ኤ.አ በ2010 ማንነቱን ይፋ ሳያደርግ በነጻ በኢንተርኔት ዘፈኖቹን በነጻ ከለቀቀ በኋላ በ2011 ሶስት የሙዚቃ ስራዎችን በመጨመር በስፋት ተደማጭነትን ማግኘት ጀመረ።

ሙዚቃ ጋር በተገናኘ ሰፊ ተደምጭነት ያላቸው እነ ፒችፎርክ (Pitchfork)፣ ኤምቲቪ (MTV)፣ ቢኢቲ (BET)፣ ሮሊንግ ስቶን (Rolling Stone)፣ ኤክስኤክስኤል (XXL) እና ዘ ሶርስ (The Source) ለአቤል ያላቸውን አድናቆት የገለጹ ሲሆን የኤምቲቪ ልዩ ዘጋቢ ጆን ኖሪስ ከማይክል ጃክሰን ቀጥሎ የመጣ ምርጥ ድምጻዊ ብሎ ሲያሞካሸው ሌላኛው የሙዚቃ ባለሙያ ኮንሲዲን አቤል እና ማይክል ድምጻቸው እንደሚመሳሰል ተናግሮ ማይክል በዛ ያሉ የብሉዝ ቅላጼዎች ሲኖሩት አቤል ደግሞ ወደ አረብኛ የሚቀርብ ቅላጼ እንዳለው ጽፏል።

ለስለስ ባሉ ዘፈኖቹ የሚታወቀው ዘ ዊኬንድ በ2012 የኤምቲቪ ኦ (MTV O) ከኢንተርኔት የተነሳ አዲስ ሙዚቀኛ ሽልማት ያሸነፈ ሲሆን በ2013 ቢኢቲ (BET) እና ቪኤምኤ (VMA) በአዲስ መጤ አርቲስት ዘርፍ ለሽልማት አጭተውታል።

የአርቲስቱን የተወሰኑ ስራዎች ተጋብዘዋል።