የማስመሰል ባለሙያዎች ፊልም ላይ የሚታይ ጉዳትን እንዲህ ነው የሚሰሩት

አንድን ፊልም በተመልካች ተወዳጅ ከሚያደርጉት ነገሮች አንዱ በሰው ዘንድ የሚታወቁ ነገሮች በፊልሙ ምን ያህል በትክክል መገለጻቸው ነው። ለምሳሌ በፊልም ላይ ያለ የካንሰር በሽተኛ ገጸባህሪ የጨረር ህክምና እየተከታተለ ቢሆን እውነተኛ አለም ላይ የሚያጋጥመውን የጸጉር መሳሳት እና መመለጥ በፊልሙም ላይ ማሳየት አስፈላጊ ነው። እንደዚህ አይነት ስራዎችን የሚሰሩ የማመሳሰል ባለሙያዎች ብዙ መንገዶች ተጠቅመው ፊልሙን ከእውነታ ጋር ያቀራርባሉ። ከታች ያለው ፊልም ላይ በአደጋ ምክንያት የሚከሰት ቁስልን ባለሙያዎቹ እንዴት እንደሚያስመስሉ ይመልከቱ።

Advertisements

የፊልም ምርጫ – ዘ ዎልፍ ኦፍ ዎል ስትሪት (The Wolf of Wall Street)

ይህ የአለማችን ትልቁ የአስዮን ድርሻ ገበያ የሆነው እና በአሜሪካን አገር ኒውዮርክ ከተማ ውስጥ ዎል ስትሪት በሚባል ጎዳና ላይ መሰረቱን ያደረገው የኒውዮርክ አክስዮን ድርሻ መገበያያ ማዕከል ውስጥ የሚሰራ ደላላ ህይወት ላይ ያጠነጠነ ፊልም ነው። በእውነተኛ ታሪክ ላይ ተመስርቶ የተሰራውን ይህንን ፊልም ዝነኞቹ ሊዮናርዶ ዲካፕሪዮ እና ማቲው ማኮግንሄይ ይተውኑበታል። የአለምን ኢኮኖሚ የሚነዳው የዚህ ማዕከል አሰራር ትንሽ ማወቅ ከፈለጉ በሚያዝናና መልኩ የሚያሳይ ፊልም ነው። የፊልሙ ማስታወቂያ ይመልከቱት።

አርቲስቶቹ ጥንዶች

Tewodros_Amleset
ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) እና አምለሰት ሙጬ

በሚያወጣቸው የተዋጣላቸው የጥበብ ስራዎቹ የህዝቡ ልብ ውስጥ ሁሌም የሚገባው አርቲስት ቴዲ አፍሮ እና ታዋቂዋ ሞዴል እና ተዋናይ ባለቤቱ አምለሰት ሙጬ በጣም የተወራለትን ጋብቻቸውን የፈጸሙት በዚህ አመት ነበር። በጓደኝነት ለረጅም ግዜ በመቆየት ግንኙነታቸው ለህዝብ ይፋ ከሆነ በኋላ ጊዜውን ጠብቀው የፈጸሙት ትዳር ለዘመኑ ወጣቶች አርአያ ነው።

tamagne_fantish

ታማኝ በየነ እና ፋንትሽ በቀለ

ቀልድን እያዋዛ ህዝቡን የሚያዝናናው ታማኝ በየነ የተለየ የመድረክ አመራር እና አጫዋችነት የተላበሰ አርቲስት ነው። ያለፉትን አመታት በፖለቲካው መስክ ጎላ ያለ ድርሻ እየያዘ ሲሆን የመዝናኛ ልምዱን ወደ ፖለቲካውም አምጥቶ እየሰራ ነው። ተጫዋች እና በሚያውቋት ሰዎች ተወዳጅ የሆነችው ባለቤቱ አርቲስት ፋንትሽ በቀለ ከሙዚቃው ራቅ ብትልም አሁንም የተወሰኑ ስራዎቿን የሚያደንቁ አይጠፉም።

bitsat_tesfaye

ብጽአት ስዩም እና ተስፋዬ ገብረሃና

ለዛ ያለው የሚስረቀረቀው ድምጿ እና በተለይ ከአርቲስት አበበ ፈቃደ ጋር በቅብብል የሚያዋዟቸው ሙዚቃዎች እና ወደ መጨረሻ ያደረሰችን አደራ ልጄን የመሳሰሉ ዘፈኖቿ መለያዎቿ ናቸው አርቲስት ብጽአት ስዩም። ባለቤቷ ተዋናይ ተስፋዬ ገብረሃናም ሰማያዊ ፈረስን ጨምሮ በርካታ ድራማዎች እና ፊልሞች ላይ የተወደደ ችሎታውን አሳይቶናል።

feker-abebe

ፍቅረአዲስ ነቃጥበብ እና አበበ ብርሃኔ

ባህላዊ ለዛ ያለው ሙዚቃዎቿ የምትታወቀው ሙዚቀኛ ፍቅረአዲስ ነቃጥበብ እና ባለቤቷ ገጣሚ እና ሙዚቀኛ አበበ ብርሃኔም በትዳር ረጀም ግዜ ቀይተዋል። አበበ ሙዚቃዎችንም በማዘጋጀት ችሎታ ያለው ሲሆን ከበርካታ አርቲስቶች ጋር በመስራትም ይታወቃል።

dagim_babi

ዳግማዊት ጸሃዬ እና ሳምሶን ታደሰ

በቅርቡ እየወጡ ካሉ በርካታ ታዋቂ አርቲስቶች መካከል ከበቂ ችሎታ እና ውጤታማነት ጋር ብቅ ያሉት ባለትዳሮች ሙዚቀኛ ዳግማዊት ጸሃዬ እና አርቲስት ሳምሶን ታደሰ (ቤቢ) ናቸው። ከአይዶል ተወዳዳሪነት በመነሳት ወደ ሙዚቃው አለም የተቀላቀለችው ዳግማዊት ወደ ፊልሙም አለም መግባት የምትችል ሲሆን ባለቤቷ ሳምሶንም በፊልም ስራዎቹ በርካታ አድናቂዎች አፍርቷል።

አርቲስት ህይወቴ አበበ ከዚህ አለም በሞት ተለየች

hiwete abebe

ባለትዳርና የአንዲት ሴት ልጅ እናት የነበረችው አርቲስት ህይወቴ አበበ  ታማ በጳውሎስ ሆስፒታል በህክምና ስትረዳ ቆይታ ነው በተወለደች በ29 ዓመቷ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች።

ሰኔ 30 1976 ዓ.ም በሃረር ከተማ የተወለደችው አርቲስት ህይወቴ አበበ በሃረር መድሃኔአለም ትምህርትቤት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን ካጠናቀቀች በኋላ አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ በመግባት የትያትር ትምህርቷን አጠናቃለች። አርቲስቷ የመቃብር ቁልፎችንና የሰርጉ ዋዜማን ጨምሮ በተለያዩ የመድረክ ቲያትሮች ላይ ሰርታለች። ባለታክሲው፣ ባለቀለም ህልሞችና ሰውዬው ፊልሞች ላይም የሰራች ሲሆን ፥ በርካታ የሬዲዮና የቴሌቪዥን ድራማዎች ላይም በመሪ ተዋናይነት ጭምር ተሳትፋለች።

ካለፉት ሶስት ወራት በፊት ጀምሮ ኑሮዋን በኡጋንዳ ካምፓላ አድርጋ የነበረችው አርቲስት ህይወቴ የቀብር ስነ ስርዓት በዛሬው እለት በአዳማ ከተማ ይፈጸማል። አራዳኦንላይን ለቤተሰቦቿ እና ለቅርብ ወዳጆቿ መጽናናትን ይመኛል።

ገመና ድራማ ወደ እንግሊዝኛ ተተርጉሞ ሊሰራ ነው

በኢትዮጲያውያን ዘንድ እጅግ ተወዳጁ ‘ገመና’ ድራማ ወደ እንግሊዝኛ ተተርጉሞ በናይጄርያ የቴሌቭዥን ጣቢያ ሊታይ ነው። አፍሪካውያን የሚቀራረብ ባህል እና ታሪክ እንዳላቸው ያስታወሰው የድራማው ተርጓሚ ናይጄሪያዊው ጆን ኦቢ ሚኬል፣ ገመና በኢትዮጲያ ውስጥ ያለውን ተቀባይነት በአፍሪካ ብሎም በአለም ላይ እንደሚያገኝ አስረግጦ ተናግሮአል። “In the house” ወደሚል እንግሊዝኛ ተከታታይ ፊልም የተተረጎመው ድራማ በናይጄሪያው NNN (Nigerian News Network) ጣቢያ ለእይታ የሚቅርብ ሲሆን በ30 ደቂቃ የሚቀርብ ተወዳጅ ተከታታይ እንደሚሆን እየተጠበቀ ነው። የፊልሙን ቀረጻ በኢትዮጲያ ለማካሄድ ፈቃድ የጠየቀው ኦቢ ሚኬል፣ ፍቃዱ ከተገኘ 40 የሚሆኑ የናይጄሪያው ኖሊውድ ባለሙያዎች እና ተዋንያን ወደ ኢትዮጲያ እንደሚያስመጣ እና ጥሩ እንግሊዝኛ ችሎታ ያላቸውን ኢትዮጲያውያንም በፊልሙ እንዲጫወቱ እድል እንደሚመቻችላቸው አስታውቋል።

Continue reading