የእግር መረብኳስ

የተለያዩ የመጠሪያ ስሞች ያሉት የእግር መረብኳስ ተብሎ የሚታወቀው ስፖርት ሶስት ሶስት ተጫዋቾች ያሏቸው ቡድኖች 1.5 ሜትር ከፍታ ላይ በተዘረጋ መረብ ተለያይተው በእግራቸው ብቻ የመረብ ኳስ የሚጫወቱበት ውድድር ነው። የተለየ መገለባበጥ ችሎታ የሚጠቀው ስፖርት በተለይ በምስራቅ እስያ በጣም ተወዳጅ ስፖርት ነው።

ካለምንም የአውሮፕላን ጉዞ የአለምን አገሮች በሙሉ የጎበኘ ሰው

በእንግሊዝ ሃገር ሊቨርፑል ከተማ ነዋሪ የሆነው ግርሃም ሂውጅስ ከብራዚል በመነሳት በተባበሩት መንግስታት እውቅና ያላቸውን ከ200 በላይ አገሮች ጎብኝቶ የመጨረሻ ጉብኝቱን ከስምንት ወራት በፊት በአዲሲቷ ሃገር ደቡብ ሱዳን አጠናቋል። ሃገሮቹን ለመጎብኘት ምንም የአውሮፕላን ጉዞ ያልትጠቀመው ግርሃም በቅርቡ ስለ ጉብኝቱ የሚያሳይ አጭር የ4 ደቂቃ ቪዲዮ አዘጋጅቷል።

ልደቱን ለእናቱ ያልታሰበ ስጦታ በማቅረብ ያከበረው ኢትዮጲያዊ

አንድ በካናዳ ነዋሪ የሆነው ኢትዮጲያዊ ከሚያገኘው አነስተኛ ገቢ በመቆጠብ የእናቱን የቤት ግዢ እዳ መክፈል የሚያችለውን ገንዘብ ማጠራቀም ችሎአል። ስጦታውን ሲሰጥ የነበረውን የእናቱን ምላሽ ከአጭር ማብራሪያ ጋር በቪዲዮ በኢንተርኔት ከለቀቀ በኋላ በርካታ አስተያየት እየደረሰው ነው። ቪዲዮውን ከስር ይመልከቱ እና አስተያየት ይስጡበት!!