ናይጄሪያ እ.ኤ.አ በ2030 ጠፈርተኛ ወደ ህዋ ለመላክ አቅዳለች

ናይጄሪያ ጠፈርተኛ

የናይጄሪያው የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ዶ/ር ኦቦናያ ኦኑ በዋና ከተማ አቡጃ እቅዱን ይፋ ሲያደርጉ እንደተናገሩት የጠፈር ምርምር ስራዎች ለሃገራቸው በጣም ጠቃሚ መሆኑን ገልጸዋል። የናይጄሪያው የጠፈር ማዕከል ባለሙያዎች ወደ ቻይና በማቅናት እቅዱን ለማሳካት ስለሚያስፈለጉ ዝግጅቶች መወያየት እንደሚጀምሩ ተናግረዋል።

የሃገሪቱ ብሄራዊ የጠፈር ምርምር እና ልማት ባለስልጣን ባለፉት 15 አመታት 5 ሳተላይቶችን ወደ ጠፈር አምጥቆ ከነዚህ ውስጥ ሶስቱ አሁንም አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ። ባለስልጣኑ ከ300 በላይ ባለሙያዎችን ይዞ እቅዱን ለማሳካት እየሰራ ሲሆን ጠፈርተኛ ከመላኩ በተጨማሪ የሃገሪቱን የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ደረጃንም አብሮ ለማሳገድ ታስቦአል። የባለስልጣኑ የግንኙነት ባለሙያ እቅዱ ከተሳካ ለናይጄሪያ ብሎም ለአፍሪካ ትልቅ ኩራት እንደሚሆን እና የአፍሪካ አገራት ጠፈር ምርምር ላይ እንዲሳተፉ እንደሚያነቃቃ ተናግረዋል።

ኢትዮጲያም ከ11 አመት በፊት በጥቂት ባለሙያዎች እና በጎ ፍቃደኞች የተቋቋመው የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ማህበርም በዘርፉ በርካታ እንቅስቃሴዎችን እያደረገ ሲይገኛል። ከነዚህም መካከል ማህበሩ በእንጦጦ ተራራ ላይ ያስተከለው የህዋ መቃኛ ቴሌስኮፕ እና በተለያዩ ዩንቨርስቲዎች ባለሙያዎችን ለማስተማር እያደረገ ያለው ጥረት ይጠቀሳሉ።[CNN]

Advertisements

ከሰውነታችን በሚመነጭ ሃይል ተንቀሳቃሽ ስልካችንን ባትሪ ሙሉ ቻርጅ ለማድረግ ምን ያህል ግዜ ይወስዳል?

አአምሮ ኤሌትሪክ

የሰው ልጅ ኤሌትሪክ ሃይል ያመነጫል? አዎ!

የአእምሮአችን እና የነርቮች አሰራር፣ በህይወት የሚያቆየን የልብ ምት እና ስራ የሚያሰራን የጡንቻዎቻችን እንቅስቃሴ በሙሉ መሰረታቸው በሰውነት ውስጥ የሚመነጭ የኤሌትሪክ ሃይል ነው። የዚህ ሃይል ዋንኛ ምንጭ ደግሞ ከምንበላው ምግብ እና ከምንጠጣው ፈሳሽ ነገር የምናገኘው  የኬሚካል ንጥረነገር ነው።

በሰውነታችን የተለያዩ ቦታዎች ከሚመረተው የኤሌትሪክ ሃይል ውስጥ በደንብ ጥናት የተደረገበት አአምሮ ውስጥ ያለው ሲሆን ይሄም በአማካይ 0.085 ዋት ይሆናል። ይህ አነስተኛ የሃይል ምንጭ ቢሆንም በየቀኑ ከምንጠቀምበት ስልክ ጋር ማገናኘት ቢቻል ባትሪውን ቻርጅ ማድረግ ይችላል።

ለምሳሌ ገበያ ላይ ከቀረበ ሁለት አመት ገደማ የሆነው ሳምሰንግ ጋላክሲ ኤስ 5 ባትሪ 10.78 ዋት-ሰዓት አቅም ሲኖረው ይህንን ባትሪ ከአአምሮአችን በሚመነጭ ኤሌክትሪክ ቻርጅ ለማድረግ

10.78/0.085 = 126.8 ሰዓት ወይም 5ቀን ከግማሽ ይፈጃል ማለት ነው። [gizmodo]

የፓሲፊቅ ውቅያኖስ በ6 አመት ውስጥ በኒውክሌር ሊመረዝ ይችላል እየተባለ ነው

8761

ከሁለት አመት በፊት በተከሰተ የማዕበል አደጋ ምክንያት በፉኩሺማ ኒውክሌር ማዕከል የሚገኙ ሶስት መቀመሚያ ጣቢያዎች በመጎዳታቸው አካባቢውንም በአቅራቢያው የሚገኘውንም ውቅያኖስ ደህንነት አደጋ ላይ ጥሎ ነበር።

በወቅቱ ማዕከሉን የሚያንቀሳቅሰው የቶኪዮ ኤሌክትሪክ ኮርፖሬሽን(ቴስኮ) ባደረገው ዳሰሳ ጉዳቱ እንደተፈራው እንዳልሆነ እና ነገሮችን በቁጥጥር ውስጥ እንደሚያደርጉ አሳውቀው ነበር። በማስከተልም የጃፓኗ ዋና ከተማ የ2020 ኦሎምፒክ ለማዘጋጀት በመጠየቅ ወሬውም ደብዝዞ ነበር። ሰሞኑን የወጡ መረጃዎች እንዳሳዩት ከሆነ እ.ኤ.አ በ2011 የተካሄደው ምርመራ ስህተቶች እንዳሉበት እና የተከሰተው የኒውክሌር መመረዝ ሰፊ ቢሆንም አንሶ እንደቀረበ ገልጸዋል።

ቴስኮም ስህተቶች እንደበሩ አምኖ አሁን መረጃዎቹን አስተካክሎ በሰፊው ለመስራት እየታሰበ እንደሆነ እና በቀየቀኑ 300 ቶን በላይ በኒውክሌር የተመረዘ ውሃ ወደ ፓሲፊክ ውቅያኖስ መሹለኩን ተናግረዋል። ችግሩን ሙሉ በሙሉ ለመቅረፍ በሚደረግ ጥረትም ተጨማሪ የተበከለ ውሃ ወደ ውቅያኖስ መግባቱ እንደማይቀር ተናግረዋል። አንዳንድ ሳይንቲስቶች መረጃዎችን አገናዝበው እንደገመቱትም በ6 አመታት ውስጥ ሙሉ ፓሲፊክ ውቅያኖስ እንደሚበከል እና በውስጡ የሚኖሩ ህይወት ያላቸው ነገሮች ስጋት ውስጥ እንደሚወድቁ ተናግረዋል።

አለቀልን!!

ለግዜው ግን ጃፓኖች ጣቢያዎቹ አካባቢ የሚገኘውን የተበከለ የውቅያኖስ ክፍል በሰው ሰራሽ መንገድ በማቀዝቀዝ እና ወደ በረዶነት በመለወጥ እንዳይስፋፋ እየሞከሩ ነው። [arirang]

ወደ ህዋ የመጠቀች ተመራማሪ መንኩራኩር ውስጥ ጸጉሯን ስታጥብ

በተደጋጋሚ ከሚደረጉት የአለም አቀፍ ህዋ ምርምር ጉዞዎች አካል በሆነ የህዋ ቡድን 36 ተጓዥ የሆነችው አሜሪካዊቷ ካረን ናይበርግ የመሬት ስበት በሌለበት መንኩራኩር ውስጥ ጸጉሯን ስታጥብ።

ማርስ ላይ መኖር ይፈልጋሉ?

ማርስዋን

ማርስዋን (Mars One) የተባለ የሆላንድ ኩባንያ እ.ኤ.አ በ2023 እንዲካሄድ ላቀደው ወደ ፕላኔት ማርስ ጉዞ የሚሳተፉ በጎ ፈቃደኞችን መመዝገብ እንደሚጀምር ዛሬ ይፋ አደረገ። ጉዞው ለየት የሚያደርገው ሰዎቹ ወደ ምድር ተመልሰው የማይመጡ ሲሆን እስከ ህይወታቸው ፍጻሜ ማርስ ላይ ለመኖር ተስማምተው ጉዞውን ይጀምራሉ።

Continue reading