ማታ ማታ ብቻ ፓራላይዝድ የሚሆኑ ፓኪስታናዊ ወንድማማቾች ጉዳይ ሃኪሞችን አስደንቋል

የ9 ዓመቱ አብዱል ራሺድ እና የ13 ዓመት ወንድሙ ሾአኢብ አህመድ

የ9 ዓመቱ አብዱል ራሺድ እና የ13 ዓመት ወንድሙ ሾአኢብ አህመድ

ሰሜን ምዕራብ ፓኪስታን በምትገኝ ኩዌታ በተሰኘች ከተማ ነዋሪ የሆኑት የ9 ዓመቱ አብዱል ራሺድ እና የ13 ዓመት ወንድሙ ሾአኢብ አህመድ በየቀኑ ማታ ማታ ላይ ሙሉ ሰውነታቸው ፓራላይዝድ ይሆን እና መናገርም መንቀሳቀስም ያቅታቸዋል። ወደ ዋናው ከተማ ኢዝላማባድ መጥተው በሃኪሞች ምርመራ ላይ ያሉት የሁለቱ ወንድማማቾች ሁኔታ ለሃኪሞችም ግራ ያጋባ ነገር ሆኖባቸዋል።

አባታቸው “ልጆቼ ቀን ቀን ከፀሃይ ሃይል ስለሚያገኙ ነው ማታ ማታ የሚደክሙት” የሚል መላ ምት አቅርበው ነበር። ነገር ግን የፓኪስታን ጤና ሳይንስ ኢንስቲትዩት ተመራማሪ ጃቬድ አክራም ሲያብራሩ ልጆቹ በቀን ፀሀይ ሳያገኙ ጨለማ ቤት ውስጥ ቢቆዩም እስካልመሸ ድረስ ጤነኛ ሆነው ስለሚንቀሳቀሱ የአባትየው ግምት ትክክል እንዳልሆነ ተናግረዋል። ከልጆቹ የደም ናሙና ተወስዶ እየተጠና ሲሆን በተጨማሪም የደጉበት አካባቡ የአየር ጸባይ መረጃ፤ የአፈር እና የአየር ናሙናም በባለሙያዎች እየተመረመረ ነው። [yahoo news]

Advertisements

ላይቤሪያ ከኢቦላ ነፃ ሆነች

ኢቦላ

ባለፈው አመት ምዕራብ አፍሪካ በተቀሰቀሰው የኢቦላ ወረርሽኝ ከ4ሺ በላይ ዜጎቿን በሞት ያጣችው ላይቤሪያ በአሁኑ ወቅት ከበሽታው ነጻ መሆኗን የአለም የጤና ድርጅት አስታወቀ። ወረርሽኙ ከመከሰቱ በፊት እራሱ አስተማማኝ የህክምና አገልግሎት ያልነበራት ላይቤሪያ ወረርሽኙ ተጨማሪ ፈተና ሆኖባት ነበር። በንክኪ የሚተላለፈው ኢቦላ የህክምና ባለሙያዎችንም ለህልፈተ ህይወት መዳረጉ ደግሞ ለበሽተኞች አስፈላጊውን እንክብካቤ ለማድረግ ሌላ አስቸጋሪ ሁኔታን ፈጥሮ ነበር።

ከኢትዮጲያ፣ ቻይና፣ ኩባ እና ሌሎች አገራት የተላኩ የህክምና ባለሙያዎች በአለም አቀፉ የጤና ድርጅት አጋዥነት በሽታውን ለመቆጣጠር ባደረጉት ጥረት ላለፉት 42 ቀናት ምንም አዲስ የኢቦላ ተጠቂ ባለመመዝገቡ አገሪቷ ከኢቦላ ነጻ መሆኗ ታውጇል።

ከላይቤሪያ በተጨማሪ ወረርሽኙ የተከሰተባቸው ጊኒ እና ሴራሊዮንም የአዲስ ተጠቂዎች ቁጥር እየቀነሰ ሲሆን ባለፈው ሳምንት ሁለቱም አገራት 9 አዳዲስ በሽተኞች ተመዝግበዋል።

ኢቦላን ለመቆጣጠር የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ የተዘጋጁ 187 ኢትዮጲያዊ የህክምና ባለሙያዎች ወደ ምዕራብ አፍሪካ አቀኑ

የህክምና ባለሙያዎቹ

የህክምና ባለሙያዎቹ

በምዕራብ አፍሪካውያኑ ላይቤሪያ፣ ሴራሊዮን እና ጊኒ የተከሰተውን የኢቦላ ወረርሽኝ የመዋጋት ሂደት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥም ቢሆን ቀስ በቀስ በጎ ነገሮች እየታየ ሲሆን ይህንን ከሚያግዙት አንዱ የአፍሪካ ህብረት እንቅስቃሴ ነው። በበሽታ የተጠቁት አገራት ኢኮኖሚያቸው አነስተኛ እና ለህዝቡ በቂ የህክምና አገልግሎት ባልተደረሰበት ሁኔታ የዚህ አስከፊ በሽታ መከሰት ሁኔታውን አደገኛ አድርጎታል። በመሆኑም ይህንን የህክምና ባለሙያ እጥረት ለመቅረፍ ከተለያዩ አገራት ባለሙያዎች ወደ አገራቱ እየገቡ ነው። በቀደምትነት ሰፊ ብዛት ያለው ባለሙያ በመላክ የአፍሪካ አጋርነቷን በድጋሚ ያስመሰከረችው ኩባ ስትሆን ቻይናና እና አሜሪካንም በወታደራዊ ሃይላቸው ድጋፍ አንዳንድ እርዳታ አያደረጉ ነው። የአፍሪካ ህብረት ከራሱ አባላት የህክምና ባለሙያዎችን ለማግኘት ባደረገው ሙከራም ኢትዮጲያ እና ናይጄሪያ በቀርቡ ባለሙያዎቻቸውን ወደዛ ልከዋል። በበጎ ፍቃደኝነት ላይ የተመሰረተ ነው የተባለው ምልመላ ተካሂዶ የተመረጡ 187 ሰዎች ወደ ላይቤሪያ እና ሴራሊዮን ተጉዘዋል። ባለሙያዎቹ ከአራት ወር ቆይታ በኋላ ሲመለሱ ለሶስት ሳምንት ጊዜአዊ ማቆያ ካረፉ በኋላ ነው ወደ ህብረተሰቡ የሚቀላቀሉት። [@tLimi]

አሜሪካ ጀማሪ ተዋንያንን ለኢቦላ መከላከያነት ልትጠቀም ነው

ኢቦላ በሽተኛ በጥንቃቄ ሲጓጓዝ

ኢቦላ በሽተኛ በጥንቃቄ ሲጓጓዝ

በ1968ዓ.ም በዛሬዋ ደቡብ ሱዳን በወረርሽኝ መልክ ለመጀመሪያ ጊዜ ከታየ በኋላ አደገኛነቱ የታወቀው የኢቦላ በሽታ በተለይ በመካከለኛው እና ምዕራብ አፍሪካ አገሮች በተለያ ጊዜያት በወረርሽኝ መልክ ተከስቷል።

አለማችን በቴክኖሎጂ ታግዛ አንድ መንደር እየሆነች በመጣችበት በአሁኑ ወቅት በላይቤሪያ፣ ጊኒ እና ሴራሊዮን የተከሰተው የኢቦላ ወረርሽን አደጋውን አለም አቀፍ አድርጎታል። እነዚህ በኢኮኖሚ ወደ ኋላ የሚባሉ አገራት ላይ የተከሰተው በሽታ ታማሚዎችን ለማከም የተዘጋጁ የህክምና ባለሙያዎችን ሳይቀር ህይወት እየቀጠፈ መሆኑ እና አስተማማኝ መድሃኒት የሌለው መሆኑ ችግሩን አስከፊ አድርጎታል። በሽታው ከተነሳበት ካለፈው ታህሳስ ጀምሮ 8ሺ የሚሆኑ ሰዎች የተያዙ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ 3ሺ 500 የሚሆኑት ህይወታቸው አልፎአል። በሽታው አሜሪካ እና አውሮፓ ውስጥም የደረሰ ሲሆን በአሜሪካ የመጀመሪያው ሞት በዚህ ሳምንት ሲመዘገብ በአውሮፓዊቷ ስፔን ደግሞ ከአፍሪካ ውጪ በሽታው ለመጀመሪያ ግዜ ከሰው ወደ ሰው ተላልፎአል።

የሰለጠኑት አገሮ የህክምና ተቋሞቻቸው ሊመጣ ለሚችል ታማሚ የሚያደርጉት ጥንቃቄ በማስቀመጥ ዝግጁነታቸውን እየፈተሹ ሲሆን አሜሪካ ይህንን ዝግጁነት ለመፈተን ጀማሪ ተዋንያንን የበሽታውን ምልክቶች በማስጠናትና ከዛም ወደ ህክምና ተቋማት በመላክ የተቋማቱን ብቃት ለመፈተን ተዘጋጅተዋል። ተዋንያኑ የሚጠበቅባቸውን ማስመሰል በሚገባ እንዲጫወቱ የሚያግዛቸውን ጽሁፍ በመመርኮዝ ሆስፒታሎችን እንዲፈትኑ የሚደረግ ሲሆን የሆስፒታል፣ የአምቡላንስ እንዲሁን የአደጋ ግዜ ሰዎች ሁሉንም ታማሚ ካልመንም ስህተት በሚገባ መያዛቸውን ይገመግማሉ። የማስመሰሉ ፈተና ለአንድ ሰአት የሚቆይ ይሆናል። [CNN]

ሸንቀጥ ያሉ ሴቶች የተሻለ ጤናማ እና የዳበረ አእምሮ እንዳላቸው በጥናት ማረጋገጡን ታዋቂው የዩንቨርሲቲ ኦፍ ኦክስፎርድ አስታወቀ።

ethiopianzxy1

በ16ሺ ሴቶች ላይ ጥናት ያደረጉት በርካታ ሳይንቲ ስቶች እንዳስረዱት ከአማካይ መጠን ተለቅ ያለ ቂጥ ያላቸው ሴቶች ከሌሎች ሲወዳደሩ የተሻለ እውቀት ባለቤት ብቻ ሳይሆኑ በሽታን የመቋቋም አቅማቸውም በዛ ያለ ነው። ጥናቱ እንዳስረዳው ጥሩ አቋም ያላቸው ሴቶች አነስተኛ የኮሌስትሮል መጠን እና ስኳርን የሚበታትን ኢንዛይም ስለሚያመነጩ በልብ ድካም እና ስኳር የመጠቃት እድላቸው አነስተኛ ነው።

ይህ ጥሩ ጎን የሚታየው በሴቶች ላይ ብቻ ሳይሆን በልጆቻቸውም ላይ እንደሆነ ተነግሯል። እናም ጥሩ ቅርጽ ካላት እናት የተወለዱ ልጆች አነስተኛ ከሆነች ሴት ልጆች የተሻሉ ጎበዞች መሆናቸውን መረጃቸው አሳይቷቸዋል።

ፕሮፌሰር ቆንስጣንጢኖስ ማኖፑሎስ በተባሉት ምሁር መሪነት የተጀመረው የኦክስፎርድ ውጤት በሌሎች ታዋቂ በሆኑ በካሊፎርኒያ እና ፒትስበርግ ዩንቨርስቲዎች በተደረጉ ጥናቶችም ታይተው ነበር። [elitedaily]

የነፍሳት መብላት ውድድር አሸናፊው ሞተ

በፍሎሪዳ ግዛት የሚገኝ አንድ የእንስሳት መሸጫ ሱቅ ባዘጋጀው የነፍሳት መብላት ውድድር ላይ የተሳተፈው የ32 አመቱ ኤድዋርድ አርክቦልድ ውድድሩን ካሸነፈ በኋላ ባጋጠመው ህመም ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል። ብዛት ያላቸው ትላትሎች በረሮዎች እና ሌሎች ነፍሳትን ከሌሎች ተወዳዳሪዎች በፍጥነት በልቶ አሸናፊነቱን ካረጋገጠ ከተወሰነ ግዜ በኋላ ነበር ህመም የተሰማው። ወዲያው የበላቸው ነገሮች ማስመለስ የጀመረው ይህ ሰውዬ እራሱን ስቶ ከተዘረረ በኋላ ወደ ሆስፒታል ቢወሰድም እስካሁን ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል። ሌሎች ተወዳዳሪዎች ተመሳሳይ መጠን ያለው ነፍሳት የበሉ ሲሆን እነሱ ምንም አይነት የህመም ምልክት እንደሌለባቸው ታውቋል። ማየት የሚችል አንጀት ካሎት የውድድሩ ፊልም ከታች ይመልከቱ።

ቤት ውስጥ በግል ኤች አይ ቪ ምርመራ ማድረግ የሚያስችል ምርት ለገበያ ቀረበ

በትላንትናው እለት የአሜሪካው የመድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ኦራ ክዊክ (OraQuick) በተባለ ድርጅት ተመርቶ ቤት ወስጥ በግል የኤች አይ ቪ (HIV) ምርምራ ማድረግ የሚያስችል ምርት ለገበያ እንዲቀርብ ፍቃድ ሰጠ። ፍቃዱን ስላገኘ በቅርቡ ወደ ገበያ የሚቀርበው ይህ መመርመሪያ በክሊኒኮች ከተለመደው ደምን መሰረት ካደረገ ምርመራ በተለየ ከአፍ ውስጥ ከሚገኝ የጉንጫችን ውስጣዊ ክፍል በስሱ ተጠርጎ በሚገኝ መረጃ ወጤቱን ያሳውቃል።

OraQuick at home HIV test

ቁጥሩ ብዙ የሆነ ሰው ኤች አይ ቪ በደማቸው ውስጥ እንዳለ የማያቅ ሲሆን እንዳይመረመሩ እንቅፋት ከሆኑ ነገሮች አንዱ ምርመራው በክሊኒክ ውስጥ መሰጠቱ እንደሆነ ታውቋል። እናም አንድ ሰው በፈለገ ግዜ እራሱን አዘጋጅቶ ምርመራ እንዲያደርግ የተዘጋጀው ይህ መመርመሪያ ውጤታማ እንደሚሆን ተገምቷል። ተመርማሪዎች የምክር እና በአጠቃቀሙ ላይ ማንኛውንም ጥያቄ እንዲያቀርቡ የስልክ እርዳታ በተጨማሪ አዘጋጅቷል ድርጅቱ።

ኤች አይ ቪ የሌለባቸውን ሰዎች 99.98% ግዜ ትክክለኛ ውጤት የሚሰጥ ሲሆን ኤች አይ ቪ ያለባቸውን ሰዎች ግን 92% ትክክለኛ ውጤት እንደሚያገኙ ታውቋል። ይህም ማለት 10000 ኤች አይ ቪ ነጻ ሰዎች 2ቱ በስህተት እንዳለባቸው ሊያሳያቸው ይችላል። እናም ባለስልጣኑም ድርጅቱም ኤች አይ ቪ ተገኝቷል የሚል ውጤት ያገኙ ተጠቃሚዎች ወደ ጤና ጣቢያ እንዲሄዱ መክሯል። [TheNewYorkTimes]

የእንቅልፍ ጥቅሞች

በቂ እንቅልፍ አግኝተው ሲነሱ የሚሰማ የመንፈስ እርጋታ እና ሰላም በሌላ በምንም ሊተካ የማይችል ነው። የሰው ልጅ በቀን ውስጥ ከ6-8 ሰአት የሚሆነውን ግዜ በእንቅልፍ ማሳለፍ እንዳለበት ተደጋግሞ ይነገራል። እንቅልፍ ሰውነታችን እና አእምሮአችን የሚያርፍበት የጤናማ ህይወት አካል እንደሆነ የሚያስረግጡት ባለሙያዎች በቂ እንቅልፍ በመተኛት የሚገኙ ጥቅሞችን ዘርዝረዋል።

Continue reading