ሉሲዎች ለሴቶች አፍሪካ ዋንጫ ማለፋቸውን አረጋገጡ።

በቅጽል ስሙ ሉሲ በሚል የሚታወቀው የኢትዮጲያ ብሄራዊ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን የታንዛንያ አቻውን በደርሶ መልስ 3 ለ 1 በማሸነፍ ኢኳቶሪያል ጊኒ ለሚካሄደው 8ኛ የአፍሪካ የሴቶች እግር ኳስ ውድድር ማለፉን አረጋገጠ። ብሄራዊ ቡድናችንን በአህጉራዊም ሆነ በአለም አቀፍ ውድድር መደገፍ ለአመታት ሲቋምጥ የነበረውን ደጋፊ ያስደሰቱት ሉሲዎች ከሳምንት በፊት በኢትዮጲያ ያገኙትን የ2-1 ድል በትላንትናው እለት በታንዛኒያም 1-0 በማሸነፍ ለአፍሪካ ውድድር አልፈዋል።

Ethiopian Women Football Team (Lucy)

የትላንቱን ጨዋታ ጠንከር ብለው የጀመሩት ትዊጋ ኮከቦች በመባል የሚታወቁት ታንዛኒያዎች ሲሆኑ ያገኟቸውን የተወሰኑ እድሎች አባክነዋል። ቀስ ብለው ወደ ጨዋታው መንፈስ የገቡት ሉሶዎች በኢትዮጲያ ውስጥ ተወዳጅ የሆነውን አጭር ቅብብል ኳስ በመጫወት ብዙ የጎል ማግባት እድሎችን ፈጥረዋል። በኤርሂማ ዘርጋ፣ ብርቱካን ገ/ክርስቶስ እና ሽታዬ ሲሳይ የሚመራው የሉሲ አጥቂዎች የታንዛንያን ተከላካይ ሲያስጨንቁ የዋሉ ሲሆን በ66ኛ ደቂቃ ብርታዊት ግርማ ባስቆጠረቻት ግብ አሸንፈው ወጥተዋል።

በርቱ ሉሲዎች!! [allafrica.com]